Directive to Provide for Income Generating Activities by Charities and Societies No. 7

For optimal readability, we highly recommend downloading the document PDF, which you can do below.

Document Information:


የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት የገቢ ማስገኛ
ስራዎች ላይ የሚሰማሩበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ
መመሪያ
ቁጥር 07/2004

መስከረም 2004 ዓ.ም

www.abyssinialaw.com


 
መግቢያ
በበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ 621/2001 አንቀጽ 103 መሰረት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት በገቢ
ማስገኛ ስራዎች ላይ መሰማራት እንደሚችሉ በመደንገጉ፤

በጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት በተለይም የገቢ ምንጫቸውን ከአገር ውስጥ የሚያገኙ በእርዳታና በሌሎች መንገዶች
ከሚያገኙዋቸው የገቢ ምንጮች በተጨማሪ በገቢ ማስገኛ ስራዎች ላይ ተሰማርተው የገቢ ምንጮቻቸውን እንዲያሰፉ
መደረግ ያለበት መሆኑ ስለታመነበት፤

በአዋጁ ስለ ገቢ ማስገኛ ስራዎች የተደነገገውን ለማስፈፀም መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት፤

የኢፌድሪ በጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ በበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ 621/2001 አንቀጽ
9/4/ እና ስለበጐ አድራጐት ድርጅቶች እና ማህበራት ምዝገባና አስተዳደር በወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር
168/2001 አንቀጽ 34 መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡ www.abyssinialaw.com


 
ክፍል አንድ
ጠቅላላ
አንቀፅ 1 አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ “የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት በገቢ ማስገኛ ስራዎች ላይ ስለሚሰማሩበት ሁኔታ ለመወሰን የወጣ
መመሪያ ቁጥር 07/2004” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
አንቀፅ 2 አውጪው አካል

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ በአዋጁና በደንቡ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

አንቀፅ 3 ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጓሜ የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር ለዚህ መመሪያ፡ –
1. “አዋጅ ” ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ ቁጥር 621/2001 ነው፡፡
2. “ደንብ ” ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት የሚንስትሮች ም /ቤት ደንብ ቁጥር 168/2001 ነው፡፡
3. “ኤጀንሲ ” ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ነው፡፡
4. “ዋና ዳይሬክተር ” ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ነው፡፡
5. “የገቢ ማስገኛ ስራ ” ማለት

አንድ የበጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማህበር በኤጀንሲው በሚሰጠው የገቢ ማስገኛ
ሥራ ፈቃድ መሠረት በበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ባለቤትነት ሥር የሆነ ለትርፍ የሚቋቋምና የበጐ
አድራጐት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ከተመዘገበበት ዓላማ እና ከተሠማራበት የሥራ መስክ ጋር ቀጥታ ግንኙነት
ያለዉና ትርፍ ለማግኘት የሚሰራ ንግድ እንቅስቃሴ ነው፡፡

6. “ፈቃድ ” ማለት በሌሎች ህጎች ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንት እና ሌሎች ትርፍ ለማግኘት ለሚሰሩ ስራዎች የተቀመጡ
የምዝገባና የፈቃድ መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆነው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት በገቢ ማስገኛ ስራዎች
ላይ ለመሰማራት እንዲችሉ በኤጀንሲው የሚሰጥ የፅሁፍ ማረጋገጫ ነው፡፡
7. በአዋጅና በማስፈፀሚያ ደንቡ ላይ የተቀመጡት ሌሎች ትርጓሜዎች በዚህ መመሪያ ላይ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
8. በዚህ መመሪያ ዉስጥ በወንድ ፆታ የተደነገገው

የሴትንም ፆታ ያካትታል፡፡

አንቀፅ 4 የተፈፃሚነት ወሰን
ይህ መመሪያ፡ –
ሀ . ከአንድ በላይ በሆኑ ክልሎች በሚሰሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማህበራት ወይም የአባላት
ጥንቅራቸዉ ከአንድ ክልል በላይ በሆኑ ማህበራት፤ www.abyssinialaw.com


 
ለ .በአንድ ክልል ብቻ የሚሰሩ ቢሆንም በዉጭ አገር በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና በኢትዮጲያ ነዋሪዎች በጎ
አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት፤እና
ሐ . በአዲስ አበባ ወይም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በሚሰሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ላይ ተፈጻሚ
ይሆናል፡፡

www.abyssinialaw.com


 
ክፍል ሁለት
ስለ ገቢ ማስገኛ ስራዎች

አንቀፅ 5. የገቢ ማስገኛ ስራ ከዓላማ ጋር ተያያዥ ስለመሆን

ገቢ የሚያስገኙ ስራዎች በጐ አድራጐት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ከሚሰራው ስራ ማንኛውም የበጐ አድራጐት ድርጅት
ወይም ማህበር በገቢ ማስገኛ ስራዎች ለመሰማራት ከሚሰራው ሥራ ጋር በቀጥታ ተያያዥነት ያለው መሆን ይገባዋል፡፡
አንቀፅ 6. የገቢ ማስገኛ ስራ ለዓላማ ማስፈፀሚያ ስለመዋሉ
1. በጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ በገቢ ማስገኛ ስራ ላይ ተሰማርቶ የሚያገኘው ትርፍ ለበጎ አድራጎት
ድርጅት ወይም ማህበር አስተዳደራዊ ወጪ መሸፈኛነት ሊውል አይችልም ፡፡
2. በበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር ስር ያለ የአስተዳደር ስራ በገቢ ማስገኛው ውስጥም በተደራቢነት
አገልግሎት የሚሰጥ በሚሆንበት ግዜ ወጪው የዋናው በጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር አስተዳደራዊ
ወጪ ተደርጐ ይወስዳል፡፡
3. የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ አስተዳደርና አስተዳደራዊ ወጪዎች ከገቢ ማስገኛ ስራው
አስተዳደርና የአስተዳደር ወጪዎች መለየት ይኖርባቸዋል፡፡
አንቀፅ 7. ከገቢ ማስገኛ ስራ የሚገኝ ትርፍ ለአባላት የማይከፋፈል
ስለመሆኑ
ከገቢ ማስገኛ ስራዎች የሚገኝ ትርፍ ለአባላት ወይም ለተጠቃሚዎች በቀጥታ በገንዘብ ወይም በቁስ ሊከፋፈል አይችልም፡፡
1. በንዑስ አንቀፅ አንድ ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ከገቢ ማስገኛ ስራ
የሚያገኘውን ትርፍ ለተጠቃሚዎች /ለአባላት/ ለሚሰጥ የበጐ አድራጐት አገልግሎት ከማዋል አያግደውም፡፡
www.abyssinialaw.com


 
ክፍል ሦስት
ስለ ገቢ ማስገኛ ሥራ ፈቃድ አሰጣጥ

አንቀፅ 8. አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች
1. በገቢ ማስገኛ ስራዎች ላይ መሰማራት የሚፈልግ የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር ለኤጀንሲው
በፅሁፍ ማመልከት ይኖርበታል፡፡
2. ለገቢ ማስገኛ ስራ የሚቀርብ ማመልካች በበጐ አድራጐት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ የበላይ አካል ወይም የስራ
ሀላፊ የሚፈረም ሆኖ፡-
ሀ / የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ስምና አድራሻ፣
ለ / የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ፣
ሐ / የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ አላማ፣
መ / የአገልግሎት ክፍያ 150 ብር፣
ሠ / የሚሰማራበት የንግድ ዘርፍ ከመነሻ ካፒታል፣
ረ / የቢዝነስ

እቅድ፣
ጋር ተያያዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
አንቀፅ 9 የገቢ ማስገኛ ሥራ ፈቃድ ይዘት
1. የገቢ ማስገኛ ስራ ከኤጀንሲው በፅሁፍ በሚሰጥ ፈቃድ ይፈቀዳል፡፡
2. የገቢ ማስገኛ ስራዎች ላይ ለመሰማራት የሚሰጥ ፈቃድ ፡ –
1/ የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር ስምና አድራሻ፣
2/ እንዲሰማራ የተፈቀደለት የገቢ ማስገኛ ስራ አይነት፣
3/ ፈቃድ የተሰጠበት ጊዜ፣ እና
4/ ለሚመለከተው የመንግስት አካል የሚሰጥ የድጋፍ ደብዳቤን
የሚያካትት ይሆናል፡፡
አንቀፅ 10. የፈቃድ ሰጪ አካል www.abyssinialaw.com


 

1. የገቢ ማስገኛ ስራ ላይ መሰማራት የሚያስችል አስፈላጊው ማጣራት ከተካሄደ በኋላ በምዝገባና ክትትል
ኦፊሰሮች አማካኝነት የሚሰጥ ይሆናል፡፡
2. የውጭ በጎ አድራጎት ድርጅቶች በገቢ ማስገኛ ስራ ላይ እንዲሰማሩ የሚሰጥ ፈቃድ በምዝገባ፣ ክትትልና
ድጋፍ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት መፅደቅ ይኖርበታል፡፡
አንቀፅ 11. ማመልከቻው ውሳኔ ስለሚያገኝበት ሁኔታ

1. የገቢ ማስገኛ ስራ ጥያቄ የቀረበለት ማንኛውም የምዝገባና ክትትል ኦፊሰር በ 15 የስራ ቀናት ውስጥ
ውሳኔውን በፅሁፍ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
2. የውጭ በጎ አድራጎት ድርጅቶች በገቢ ማስገኛ ስራ ላይ እንዲሰማሩ የሚሰጥ ፈቃድ በምዝገባና
ክትትል ኦፊሰር ከተመረመረ በኋላ የምዝገባ፣ ክትትልና ድጋፍ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት በ 10 የስራ
ቀናት ውስጥ መፅደቅ ይኖርበታል፡፡
አንቀፅ 12. ገቢ ማስገኛ ስራ ላይ ለመሰማራት ብቁ የሚያደርጉ መመዘኛዎች
የገቢ ማስገኛ ስራ ላይ ለመሰማራት የሚቀርብ ማመልከቻ ላይ ውሳኔ ሲሰጥ ኤጀንሲው የሚከተሉትን ጉዳዮቸ ከግምት
ሊያስገባ ይችላል፡ –
1. የበጐ አድራጐት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ አላማውን ለማሳካት ከተመዘገበበት ዓላማና ከተሰማራበት
የስራ መስክ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት ያለዉ መሆኑን፤
2. የበጐ አድራጐት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ በተመዘገበበትና ፈቃድ ባገኘበት ዓላማ መሠረት እየተንቀሳቀሰ
የሚገኝ ከሆነ፣
3. ለመሰማራት ጥያቄ የቀረበበት የገቢ ማስገኛ ስራ ከመልካም ስነ -ምግባር ጋር ተቃራኒ ያልሆነ መሆኑን፤
4. በአዋጁና በደንቡ እንዲሁም በሌሎች ህጎች የተቀመጡ ግዴታዎችን አክብሮ በመሥራት የተሻለ
አፈፃፀም መኖር፤

አንቀፅ 13. የአቤቱታ ሥነ ሥርዓት
1. በዚህ መመሪያ አንቀጽ 10 ንዑስ አንቀጽ 1 በተሰጠዉ አገልግሎት ላይ ቅር የተሰኘ ተገልጋይ በ5 የሥራ ቀናት
ዉስጥ ለምዝገባ፣ ክትትልና ድጋፍ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት ቅሬታዉን በጽሑፍ ማቅረብ ይችላል፡፡ www.abyssinialaw.com


 
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 በተሰጠዉ ዉሳኔ ላይ ቅሬታ ያለዉ ተገልጋይ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን
ለኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ማቅረብ ይችላል፡፡
3 በዚህ መመሪያ አንቀጽ 10 ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት ለዉጭ የበጎ አድራጎት ድርጅት በተሰጠዉ አገልግሎት ላይ
ቅር የተሰኘ ተገልጋይ በ 5 የሥራ ቀናት ዉስጥ ቅሬታውን ለኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር በጽሑፍ ማቅረብ
ይችላል፡፡

አንቀፅ 14. ስለ የንግድ ፈቃድና ሌሎች ሁኔታዎች

1. ገቢ የሚያስገኙ ስራዎች ላይ ለመሰማራት የጠየቀው የበጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማህበር
ከኤጀንሲው በፅሁፍ ፈቃድ ካገኘ በኋላ ትርፍ በሚያስገኙ ስራዎች ላይ ለመሰማራት የሚያስችለውን
የንግድ ፈቃድ ከተገቢው የመንግስት አካል ዘንድ ቀርቦ ማግኘት ይኖርበታል፡፡
2. በዚህ መመሪያ ስለ ገቢ ማስገኛ ስራዎች የተደነገጉት እንደተጠበቁ ሆነው በንግድና ኢንቨስትመንቱ
እንዲሁም ትርፍ ለማግኘት በተቋቋሙ ድርጅቶች ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ የምዝገባ፣የፈቃድ፣የግብርና
ሌሎች ግዴታዎች በሙሉ በገቢ ማስገኛ ስራዋችም ላይ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
3. የበጐ አድራጐት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ የገቢ ማስገኛ ስራዎችን ለመስራ

ት ከንግድና ኢንቨስትመንት
ጋር በተያያዘ በሌሎች ህጐች መሠረት የሚያገኛቸውን ማናቸውም የፈቃድ ሰርተፍኬቶች፣ የግብር መለያ
ቁጥርና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ወዲያውኑ ለኤጀንሲው ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
4. የበጐ አድራጐት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ገቢ በሚያስገኝ ስራ ላይ ለመሰማራት የሚያወጣው የንግድ
ፈቃድም ሆነ የሚ

ያገኛቸው ማናቸውም መብቶች ፀንተው የሚቆዩት የበጐ አድራጐት ድርጅቱ ወይም
ማህበሩ ህጋዊ ሰውነቱ ተጠብቆ እስከሚቆይበት ጊዜ ብቻ ነው፡፡
አንቀፅ 15. ስያሜን በሚመለከት
1. የበጐ አድራጐት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ የገቢ ማስገኛ ስራ የንግድ ፈቃድ ስም ከበጐ አድራጐት
ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ስም የተለየ መሆን ይኖርበታል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 እንደተጠበቀ ሆኖ ስያሜን በሚመለከት በንግድ ሚኒስቴር ህግ መሠረት
ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

www.abyssinialaw.com


 
ክፍል አራት
ስለ ሂሳብ አያያዝና ገንዘብ አጠቃቀም

አንቀፅ 16. ስለ ሂሳብ መዝገብ

1. ገቢ የሚያስገኙ ስራዎችን የሚሰራ የበጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማህበር ገቢ የሚያስገኙ ስራዎችን
በተመለከተ ከበጐ አድራጐት ስራው የተለየ የሂሳብ መዛግብት መያዝ ይኖርበታል፡፡
2. ገቢ ማስገኛ ስራውን በተመለከተ የሚያዘው የሂሳብ መዝገብ በንግድ፣ ኢንቨስትመንት እንዲሁም
በግብር ህጐች ላይ የተዘረዘሩትን የሂሳብ መዝገብ አያያዝ መስፈርቶች ያሟላ መሆን ይኖርበታል፡፡
3. የገቢ ማስገኛ ስራው የባንክ ሂሳብ ከበጐ አድራጐት ድርጅቱ ወይም ማህ
በሩ ሂሳብ የተለየ መሆን
ይገባዋል፡፡
4. የገቢ ማስገኛ ስራ የባንክ ሂሳብ ለመክፈት ለኤጀንሲው ማሳወቅና ፈቃድ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡
አንቀፅ 17. ስለ ገንዘብ አጠቃቀም
1. ገቢ የሚያስገኙ ስራዎችን ለመስራት የሚውል የምዝገባ ጉዳይ ማስፈፀሚያና የገቢ ማስገኛ ስራው
ማስጀመሪያ ካፒታል በበጐ አድራጐት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ወጪ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
2. የገቢ ማስገኛ ስራው ተቋቋሞ ስራ ከጀመረ በኋላ የሚካሄድ ማናቸውም አይነት የገንዘብ እንቅስቃሴዎች
በጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማህበር የገንዘብ እንቅስቃሴ ጋር ግንኙነት ያላቸው መሆን
የለባቸውም፡፡
3. የገቢ ማስገኛ ስራው ወጪና ኪሳራ በንግድ ህግ አግባብ መሠረት ከተሰላ በኋላ የሚገኝ የተጣራ ትርፍ
በገቢ ማስገኛ ስራው የሂሳብ ሠራተኛ አማካኝነት ወደ በጐ አድራጐት ድርጅቱ ወይም ማህ

በሩ ሂሳብ
እንዲገባ መደረግ ይኖርበታል፡፡

አንቀፅ 18. አስተዳደራዊ ጉዳዮች
1. የገቢ ማስገኛ ስራ አስተዳደር ከበጐ አድራጐት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ የተለየና የለት ተለት
ስራዎችን የሚያከናውን ስራ አስኪያጅና የሂሳብ ሹም ሊኖረው ይገባል፡፡
2. ከላይ በንዑስ አንቀፅ 1 ላይ የተጠቀሰው ቢኖርም የበጐ አድራጐት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ የገቢ
ማስገኛ ስራውን በበላይነት ከመቆጣጠር የሚያግደው አይሆንም፡፡
አንቀፅ 19. ስለ መፍረስ www.abyssinialaw.com


 
1. የገቢ ማስገኛ ስራው በኪሳራ የበጐ አድሪጐት ድርጅቱ ወይም ማህበር ውሳኔ ወይም በኤጀንሲው ውሳኔ
እንዲዘጋ /እንዲፈርስ/ በሚደረግበት ጊዜ የባለዕዳዎች መብት ተከብሮ ሀብትና ንብረት ወደ በጐ
አድራጐት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ እንዲተላለፍ ይደረጋል፡፡
2. የገቢ ማስገኛ ስራው የሚዘጋበት ምክንያት በበጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማህበሩ ህጋዊ ሰውነት
ማብቃት ምክንያት በሚሆንበት ግዜ የባለዕዳዎች መብት ተከብሮ ሀብትና ንብረት በኤጀንሲው ውሣኔ
ለተመሳሳይ ዓላማ ላላቸው ድርጅቶች ይሆናል፡፡
3. የገቢ ማስገ

ኛ ስራው ሲፈርስ የሚነሱ የንብረት ክፍፍል ጥያቄዎችን በሚመለከት በበጐ አድራጐት
ድርጀቶችና ማህበራት ኤጀንሲ መመሪያ ቁጥር 06/2003 መሠረት የሚፈፀም ይሆናል፡፡
አንቀፅ 20. ስለ ሪፖርት አቀራረብ
1. የበጐ አድራጐት ድርጅቶች ወይም ማህበራት ከበጐ አድራጐት ድርጅቱ ወይም ማህበር መደበኛ ሪፖርት
የተለየና የገቢ ማስገኛ ስራውን የገንዘብ እንቅስቃሴ ሊያሳይ የሚችል አመታዊ የኦዲት ሪፖርት
ለኤጀንሲው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. የኦዲት ሪፖርት አቀራረብና ይዘትን በተመለከተ በኤጀንሲው መመሪያ ቁጥር —2004 ስለኦዲት ሪፖርት
የተደነገጉት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

www.abyssinialaw.com

10 
 
ክፍል አምስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
አንቀፅ 21. ስለ ቅጣት
1 ማንኛውም የበጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማህበር፡-
ሀ / በዚህ መመሪያ መሠረት ከኤጀንሲው ፈቃድ ሳያገኝ በገቢ ማስገኛ ስራ ላይ ተሰማርቶ የተገኘ እንደሆን፤
ለ / በዚህ መመሪያ ከተደነገገው አግባብ ውጪ በገቢ ማስገኛ ስራው የሚያገኘውን ትርፍ ለተጠቃሚዎች
ወይም ለአባላት ያከፋፈለ እንደሆነ፤
ሐ / ለገቢ ማስገኛ ስራዎች የተለየ የሂሳብ መዛግብት ያልያዘ፣ የተለየ ሂሳብ ቁጥር ያልከፈተ፣ የገንዘብ
እንቅስቃሴውን ከበጐ አድራጐት ድርጅት ወይም
ማህበር የቀላቀለ እንደሆነ፤
መ / ለመልካም ስነ -ምግባር ተቃራኒ የሆነ የገቢ ማስገኛ ስራ ላይ ተሰማርቶ እንደሆነ፤
ሠ / ከገቢ ማስገኛ ስራው የሚያገኘውን ገቢ ለዋናው በጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማህበር አስተዳደራዊ
ወጪ መሸፈኛነት ያዋለው እንደሆነ፤
እንደነገሩ ሁኔታና እንደጉዳይ ክብደት ኤጀንሲው ከፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ፈቃድ ስረዛ ያሉ እርምጃዎችን ሊወስድ
ይችላል፡፡
2. በዚህ
አንቀፅ ንኡስ አንቀፅ 1 የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ከወንጀል ጋር የተያያዙ ተግባራት በወንጀል ህግ
ድንጋጌዎች መሰረት የሚያስቀጡ ይሆናል፡፡
አንቀፅ 22. የመሸጋገሪያ ድንጋጌዎች
1. ከዚህ መመሪያ መውጣት በፊት በገቢ ማስገኛ ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ በጐ አድራጐት ድርጅቶችና
ማህበራት ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 እንደተጠበቀ ሆኖ ቀደም ሲል የኤጀንሲውን ፈቃድ ሳያገኙ እንዲሁም የንግድ ፈቃድ
ሳያገኙ በገቢ ማስገኛ ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ በጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት በዚህ መመሪያ መሰረት
እስከ 6 ወር ጊዜ ወስጥ አስፈላጊውን ፈቃድ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡

3.
የንግድ ፈቃድ አግኝተው የንግድ ስራ እየሰሩ ያሉ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማህበራት ይህ መመሪያ
ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ እስከ 6 ወር ጊዜ ዉስጥ በኤጀንሲው ቀርበው ከመመሪያው ጋር በተጣጠመ መልኩ
ራሳቸውን ማደራጀት ይገባቸዋል፡፡

አንቀፅ 23. መመሪያው ስለሚሻሻልበት ሁኔታ www.abyssinialaw.com

11 
  ኤጀንሲው
ይህንን መመሪያ ተግባራዊ ሲያደርግ የሚከሰቱ ክፍተቶችን ለመሙላት፣ አዋጁንና ደንቡን የሚጠቀም ሆኖ
ሲያገኘዉ በማንኛዉም ጊዜ ሊያሻሽለው ይችላል፡፡

አንቀፅ 24. ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው ሌሎች ህጎች
ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማንኛውም መመሪያና ልማዳዊ አሰራር ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡
አንቀፅ 25. መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ
ይህ መመሪያ በኤጀንሲው ፀድቆ ከወጣበት ከመስከረም 13 ቀን 2004 ዓ ም ጀምሮ ተፈፃሚነት ይኖረዋል፡፡
አሊ ሲራጅ መሀመድ
የበጎ አደራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ
ዋና ዳይሬክተር www.abyssinialaw.com