Directive to Provide for Public Collection by Charities and Societies No. 5

For optimal readability, we highly recommend downloading the document PDF, which you can do below.

Document Information:


የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኀበራት ህዝባዊ
መዋጮ የሚሰበሰቡበትን ሁኔታ ለመወሰን
የወጣ መመሪያ

ቁጥር 5/2003

ሐምሌ 9/2003 ዓ.ም
አዲስ አበባwww.abyssinialaw.com


 

መግቢያ
በበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማኀበራት አዋጅ 621/2001 ከ አንቀጽ 98- 101 ስለ ህዝባዊ መዋጮ
የተደነገገውን በስራ ላይ ለማዋል የሚያስችል ዝርዝር መመሪያ የማዘጋጀቱ አስፈላጊነት ስለታመነበት፤

በጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት የሀገር ውስጥ የገቢ ምንጫቸውን ለማሳደግ ህዝባዊ መዋጮ
የሚያከናውኑበትን መንገድ ማመቻቸት እንዲሁም ህዝባዊ መዋጮ የማሰባሰቡን ሂደት ግልጽ እና ሐላፊነት
የተሞላበት መሆኑን ለማረጋገጥ ያስችል ዘንድ የሂደቱን ዝርዝር ሁኔታ መወሰን በማስፈለጉ፤

የኢፌድሪ

በጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ በበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ
621/2001 አንቀጽ 9/4/ እና ስለበጐ አድራጐት ድርጅቶች እና ማህበራት ምዝገባና አስተዳደር በወጣው
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 168/2001 አንቀጽ 34 መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

www.abyssinialaw.com


 
ክፍል አንድ
ጠቅላላ
አንቀጽ 2. አውጭው አካል
የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማኀበራት ኤጀንሲ በበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራትን ለመመዝገብና ለማስዳደር
በወጣው አዋጅ ቁጥር 621/2001 አንቀጽ 9/4/ እና ስለበጐ አድራጐት ድርጅቶች እና ማኀበራት ምዝገባና አስተዳደር
በወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 168/2001 አንቀጽ 34 በተሠጠው ስልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ
አውጥቷል፡፡
አንቀፅ 2 አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ “ የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ሕዝባዊ መዋጮ የሚያሰባስቡበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ”
ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
አንቀፅ 3 ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጓሜ የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር ለዚህ መመሪያ ዓላማ፡-
1. “ አዋጅ ” ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራትን ለመመዝገብና ለማስተዳደር የወጣ አዋጅ ቁጥር 621/2001
ነው፡፡
2. “ ደንብ” ማለት ስለበጐ አድራጐት ድርጅቶች እና ማህበራት ምዝገባና አስተዳደር የወጣ የሚንስትሮች ም /ቤት ደንብ
ቁጥር 168/2001 ነው፡፡
3. “ኤጀንሲ ” ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ነው፡፡
4. “ቦርድ” ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ቦርድ ማለት ነው፡፡
5. “ ዋና ዳይሬክተር ” ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ነው፡፡
6. “ ሕዝባዊ መዋጮ” ማለት በሕዝባዊ ወይም በሥራ ወይም በመኖሪያ ቦታዎች በመሄድ የሚገኘውን ገቢ ለበ


አድራጎት ተግባሮች እንደሚያውለው ገልጾ ገንዘብ ወይም ሌላ ንብረት በዋጋ ወይም በነጻ ለማሰባሰብ የሚደረግ
ጥሪ ማለት ሲሆን ለሀይማኖት ወይም ለቀብር አገልግሎት በዋለ መሬት ወይም ሕንጻ ወይም አጠገባቸው ባለ
መሬት ላይ የሚደረግ ጥሪን አያጠቃልልም፤
7.

“ የውጭ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ” ማለት በውጭ ህግ መሰረት የተቋቋመ ወይም የውጭ ዜጎች በአባልነት ያሉበት
ወይም ከውጭ ምንጭ የሚገኝ ገቢ የሚጠቀም ወይም የውጭ ዜጎች የሚቆጣጠሩት የበጎ አድራጎት ድርጅት
ነው፤
8. በአዋጁ እና በደንቡ የተሰጡ ትርጓሜዎች ለዚህ መመሪያም ተፈፃሚ ይሆናሉ ፡፡
9. በዚህ መመሪያ ውስጥ ለወንድ ፆታ የተገለጸው አነጋገር ሴትንም ይጨምራል፡፡
www.abyssinialaw.com


 
አንቀፅ 3 የተፈፃሚነት ወሰን
ይህ መመሪያ
ሀ . ከአንድ በላይ በሆኑ ክልሎች በሚሰሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማህበራት ወይም የአባላት ጥንቅራቸው ከአንድ
ክልል በላይ በሆኑ ማህበራት፤
ለ . በአንድ ክልል ብቻ የሚሰሩ ቢሆንም በውጭ አገር በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና በኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት
ድርጅቶችና ማኀበራት፤
ሐ . በአዲስ አበባ ወይም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በሚሰሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኀበራት፤
መ . በአዋጁ አንቀጽ 48

መሰረት በኤጀንሲዉ ቀርበው የማጽደቅ ውሳኔ የተሰጣቸው የበጎ አድራጎት ኮሚቴዎች ላይ ተፈጻሚ
ይሆናል፡፡

www.abyssinialaw.com


 
ክፍል ሁለት
ስለ ፈቃድ አሰጣጥ

አንቀፅ 4 የፈቃድ ሰጪ አካል
1. ህዝባዊ መዋጮ ለማካሄድ የሚያስችለው ፈቃድ በኤጀንሲው አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸው
ከተረጋገጠ በኋላ በምዝገባና ክትትል ኦፊሰሮች አማካኝነት የሚሰጥ ይሆናል፡፡
2. የውጭ በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና የኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ህዝባዊ መዋጮ
እንዲያካሂዱ የሚሰጥ ፈቃድ በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር መፅደቅ ይኖርበታል ::

አንቀፅ 5 አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች
1. ህዝባዊ መዋጮ ለማካሄድ የሚፈልግ በጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማኀበር መዋጮው ሊካሄድ ከታሰበበት ቀን 1
ወር ቀደም ብሎ ለኤጀንሲው በፅሁፍ ማመልከት ይኖርበታል፡፡
2. ህዝባዊ መዋጮ ለማካሄድ ፈቃድ ለማግኘት የሚቀርብ ማመልከቻ በበጐ አድራጐት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ
የበላይ አካል ወይም የስራ ሀላፊ የሚፈረም ሆኖ የሚከተሉትን መያዝ ይኖርበታል፡ –
1. የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ስምና አድራሻ፤
2. የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ፤
3. የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ዓላማ፤
4. ሕዝባዊ መዋጮ የሚደረግለት የበጎ አድራጎት ዓላማ፤
5. ህዝባዊ መዋ

ጮውን ለማድረግ የተወሰነበት ምክንያት እና ህዝባዊ መዋጮ ማድረጉ ዓላማውን
ለማሳካት ያለው ጠቀሜታ፤
6. ሕዝባዊ መዋጮው የሚካሄድበትን ቦታ፤
7. ህዝባዊ መዋጮው የሚጀመርበትና የሚጠናቀቅበትን ቀን እና ሰዓት፤
8. ሕዝባዊ መዋጮው የሚካሄድበትን ዘዴ፤
9. ሕዝባዊ መዋጮውን በበላይነት የሚመራውን/

የሚመሩትን የስራ መሪ /የስራ መሪዎች ወይም
ግለሰብ /ግለሰቦች የሚመለከት መረጃ፤
10. ህዝባዊ መዋጮውን ለማካሄድ የሚያስችል የፋይናንስና የአፈፃፀም የድርጊት መርሃ ግብር፤
11. በህዝባዊ መዋጮው ሊገኝ የታቀደው የገቢ መጠን፤ እና
12. ሌሎች በኤጀንሲው የሚጠየቁ ተያያዥ መረጃዎች፡፡
3. በህዝባዊ መዋጮ የሚሰበሰበው ሃብት ከአገር ውጭ ላለ የበጎ አድራጎት ተግባር ሊውል የሚችልበት ሁኔታ ሲኖር
ሕዝባዊ መዋጮው ያለ

ኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ይሁንታ ሊፈቀድ አይችልም፡፡
4. በዚህ አንቀፅ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የውጭ በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት
ድርጅቶችና ማህበራት የህዝባዊ መዋጮ ለማካሄድ ፈቃድ ሊሰጠው የሚችለው ድርጅቱ ዓላማውን ለማሳካት www.abyssinialaw.com


 
ህዝባዊ መዋጮ ማድረጉ የመጨረሻ አማራጭ መሆኑን ኤጀንሲው ሲያምንበት እና ከሚያካሂደው መዋጮ
የሚሰበሰበው ገቢ በሃገር ውስጥ ላለ የበጎ አድራጎት ተግባር የሚውል ከሆነ ብቻ ነው፡፡

አንቀፅ 6 የፈቃድ ይዘት
1. ህዝባዊ መዋጮ የማካሄድ ፈቃድ ከኤጀንሲው በፅሁፍ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
2. ህዝባዊ መዋጮ ለማካሄድ የሚሰጥ ፈቃድ የኤጀንሲው ማህተም ያረፈበት ሆኖ፡-
1. የበጎ አድራጎት ድርጅቱን ወይም የማህበሩን ስምና አድራሻ፤
2. ህዝባዊ መዋጮ የሚከናወንባቸው መንገዶች፤
3. የመዋጮ ስብሰባው እንዲያካሂድበት የተፈቀደለትን ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት፤
4. አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የተደረጉ ገደቦችን ወይም ክልከላዎችን፤
5. ፈቃዱ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ፤
6. ለህዝባዊ መዋጮው የሚመለከታቸው አካላት ትብብር እንዲያደርጉ የሚገልፅ መግለጫን
የሚያካትት ይሆናል፡፡
3. የህዝባዊ መዋጮ ፈቃድ እንደነገሩ ሁኔታ ከመዋጮ ስብሰባው ቦታ፣ ባህሪ፣

ዓይነት ዘዴ፣ ቀን፣ ጊዜ ወይም የጊዜ
ርዝመት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ገደቦች ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡
አንቀፅ 7 ማመልከቻው ውሳኔ ስለሚያገኝበት ሁኔታ
1 ህዝባዊ መዋጮ ለማካሄድ ማመልከቻ የቀረበለት የምዝገባና ክትትል ኦፊሰር ህዝባዊ መዋጮ ለማቅረብ የቀረበውን
ጥያቄ ተገቢነት እና የመረጃዎቹ ተሟልቶ መቅረብ ግምት ውስጥ በማስገባት በ 15 የስራ ቀናት ውስጥ ውሳኔውን
በፅሁፍ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
2 የውጭ በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና የኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት በህዝባዊ መዋጮ ስራ ላይ
እንዲሰማሩ የሚሰጥ ፈቃድ በምዝገባና ክትትል ኦፊሰር ከተመረመረ በኋላ በ 5 የስራ ቀናት ውስጥ በኤጀንሲው ዋና
ዳይሬክተር ውሳኔ ያገኛል፡፡
አንቀጽ 8 ለህዝባዊ መዋጮ ብቁ የሚያደርጉ መመዘኛ መስፈርቶች
ኤጀንሲው የህዝባዊ መዋጮ ፈቃድ ለማግኘት የሚቀርብ ማመልከቻ ላይ የሚከተሉትን ጉዳዮች ከግምት
ሊያስገባ ይችላል፡ –
1. ጥያቄው ሕግንና ሰላምን የማይፃረር መሆኑ፤
2. ዓላማውን ለማሳካት አስፈላጊ መሆኑ፤
3. በአዋጁ፣ በደንቡና ሌሎች መመሪያዎች ላይ የተቀመጡ ግዴታዎችን በመፈፀም የተሻለ አፈፃፀም መኖሩን፤
4. ዓላማውን ለማሳካት ከሌሎች ምንጮች ገቢ የማግኘት ዕድል ጠባብ መሆኑ፤ www.abyssinialaw.com


 
አንቀጽ 9 ፈቃድ ስለመከልከል
1. በአዋጁ አንቀጽ 100 የተቀመጡት ፈቃድ የመከልከያ ምክንያቶች እንዲሁም በአንቀጽ 101 የተቀመጡት ፈቃድ
የመሰረዣ ምክንያቶች እንደተጠበቁ ሆነው ኤጀንሲው ፈቃድ በሚሰጥበት ጊዜ፡ –
ሀ . የህዝብ መዋጮ ሊሰበሰብበት የታቀደበት ዘዴ፣ ቀን፣ የመዋጮ አሰባሰቡ ድግግሞሽ ወይም የታሰበው ቦታ
በህብረተሰቡ ላይ አላስፈላጊ ጫናን የሚፈጥር ነው ብሎ ሲያምን፤
ለ . የህዝባዊ መዋጮ እንዲካሄድበት የተፈቀደበት ሁኔታ ከሌላ በጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር ተግባር
ጋር መደራረብ የሚፈጥር ከሆነ፤
ሐ . ህዝባዊ መዋጮ ማሰባሰቢያ ዘዴው ውጤታማነት አጠራጣሪ ሆኖ ሲገኝና ለመዋጮው ማከናወኛ
የሚወጣው ገንዘብ

ከሚገኘው ገቢ አንፃር የተጋነነ ሆኖ ሲገኝ፤
መ . በጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ከዚህ ቀደም የተሰጠውን የህዝባዊ መዋጮ ፈቃድ ግዴታዎቹን
ያልተወጣ ከሆነ፤
ሠ . ሕዝባዊ መዋጮ ያቀረበው የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር ከዚህ ቀደም ህግን በማጣሱ ምክንያት

በኤጀንሲውና በሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እርምጃ ተወስዶበት ከሆነ፤
ረ . የሕዝባዊ መዋጮውን ስራ እንዲያስተባብሩ በበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ሃላፊነት የተሰጣቸው
ግለሰቦች መልካም ስነ -ምግባር የሌለው መሆኑ ሲረጋገጥ፣ ከዚህ በፊት ታማኝነትን ከማጉደልና
ከማጭበርበር ድርጊቶች እንዲሁም ሃላፊነት በአግባቡ ካለመወጣት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች
ተፈርዶባቸው ወይም አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶባቸው ያውቅ እንደሆነ፤
ፈቃዱን በከፊል ወይም በሙሉ የመከልከል፣ ለሌላ ጊዜ የማስተላለፍ ወይም ሊሟሉ የሚገባቸውን
ቅድመ ሁኔታዎች
በማስቀመጥ ፈቃዱን የመስጠት ስልጣን ይኖረዋል ::
2. ኤጀንሲው ፈቃዱን ከሰጠ በኋላ ፈቃዱን የሰጠበት ሁኔታዎች የተለዋወጡ እንደሆነ ወይም ሊለዋወጡበት
የሚችሉበት ሁኔታ ከተፈጠረ የሰጠውን ፈቃድ ለተወሰነ ጊዜ የማገድ፣ የመሰረዝ ወይም ያስቀመጣቸውን ቅድመ
ሁኔታዎች ይዘት መለወጥ ይችላል፡፡
3. በዚህ አንቀፅ 2 መሰረት ኤጀንሲው የሰጠውን ፈቃድ ሲከለክል ወይም ያስቀመጣቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ሲቀይ

ለበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ውሳኔውን ከነምክንያቶቹ በጽሁፍ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ www.abyssinialaw.com


 
አንቀፅ 10 የአቤቱታ ስነ ሰርዓት
በህዝባዊ መዋጮ የመሰብሰብ ፈቃድ አሰጣጥ ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም አመልካች ውሳኔው በደረሰው 10 የስራ ቀናት
ውስጥ ተገቢውን የኤጀንሲውን የአስተዳደር እርከን ተከትሎ የመጨረሻ ቅሬታውን ለኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ማቅረብ
ይችላል፡፡

www.abyssinialaw.com


 
ክፍል ሦስት
ስለመዋጮ አሰባሰብ ስርዓት

አንቀጽ 11 የህዝባዊ መዋጮውን መሰብሰብ ስለሚችሉ አካላት
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት አካላት ፈቃድ በተሰጠው የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር ስም የህዝባዊ መዋጮ ማካሄድ
ይችላሉ፡ –
1. የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ሰራተኞች፤
2. በበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ውስጥ በበጎ ፈቃደኘነት የሚያገለግሉ ግለሰቦች፤
3. የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ተጠቃሚዎች፤ እና
4. በበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ህጋዊ ውክልና የተሰጣቸው አካላት፡፡

አንቀጽ 12 የህዝባዊ መዋጮ ሰብሳቢው የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር ግዴታዎች

1. ማንኛውም የህዝባዊ መዋጮ ለመሰብሰብ ፈቃድ ያገኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር መዋጮ እንዲሰበስብ
ያሰማራው ወይም የወከለው ሰው በዚህ መመሪያም ሆነ በሌሎች ተመሳሳይ ህጎች የተቀመጡ ደንቦችን አክብሮ
እንዲንቀሳቀስ ኃላፊነቱን ወስዶ የመከታተል ግዴታ አለበት፡፡
2. ማንኛውም የህዝባዊ መዋጮ ለመሰብሰብ ፈቃድ ያገኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር መዋጮ እንዲሰበስብ
ያሰማራው ወይም የወከለውን ሰው ስም እና ሙሉ አድራሻ መዝግቦ የመያዝ
እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላቱን
ማረጋገጥ አለበት፡-
1. እድሜው ከ 18 ያላነሰ፤
2. የዚህን መመሪያ ይዘት እንዲሁም በመዋጮ ስብሰባ ጊዜ የተከለከሉ ድርጊቶችን ጠንቅቆ የሚያውቅ፤ እና
3. እንደ መዋጮው ሁኔታ መዋጮውን ለመሰብሰብ አካላዊና ስነ -ልቦናዊ ብቃት ያለው፤
4. በህግ ክልከላ ያልተደረገበት፤
3. የህዝባዊ መዋጮውን የሚያካሂደው የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር መዋጮውን እንዲሰበሰቡ የሚያሰማራቸው
ሰዎች፡ –
1. የበጎ አድራጎት ድርጅቱን ወይም ማህበሩን እና የሰብሳቢውን ግለሰብ ስም በግልጽ የሚያሳይ፣ የመዋጮው
አስተባባሪ ፊርማ እና የድርጅቱ ወይም ማህበሩ ማህተም የያዘ የደረት መለያ፤
2. ህዝባዊ መዋጮውን የሚያካሂደው የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር

ማህተም ያረፈበት ከኤጀንሲው
የተሰጠ የህዝባዊ መዋጮ ፈቃድ ደብዳቤ ወይም ሰርተፍኬት ቅጅ፤ እንዲይዙ ማድረግ ይገባዋል፡፡
4. መዋጮው የሚሰበሰበው በፖስ

ታ፣ በካርኒ ወይም በሳጥን በሚሆንበት ጊዜ ሁሉም ፖስታዎች፣ ካርኒዎች ወይም
ሳጥኖች የራሳቸው መለያ ቁጥር ያላቸው ሳጥኖች የበጎ አድራጎት ድርጅቱን ወይም ማህበሩን ስም፣ አርማ እና ማህተም
እንደያዙ ማረጋገጥ አለበት፡፡ www.abyssinialaw.com


 
5. መዋጮው ከተሰበሰበ በኋላ መዋጮው የተሰበሰበበት ፖስታ ወይም ሳጥን መከፈት የሚችለው ድርጅቱን ወይም
ማህበሩን ወይም ሕዝባዊ መዋጮውን በበላይነት የሚመራው የስራ መሪ ወይም ተወካይ ሰው ፊት ብቻ ነው፡፡
6. በመኖሪያ ቤት እና በተከለሉ ቦታዎች የሚደረግ ማንኛውም የህዝባዊ መዋጮ ማሰባሰብ ስራ ከኤጀንሲው የተለየ
ፈቃድ ካልተሰጠ በስተቀር ከጧቱ 1፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት ብቻ ሊደረግ ይገባል፡፡
7. የኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማህበራት ወይም ህብረቶቻቸው የህዝባዊ መዋጮ ስብሰባውን
በሚያካሂዱበት ወቅት ገቢ እንዲያገ

ኙ ካልተፈቀደላቸው ከውጭ ምንጮች ከአጠቃላይ ዓመታዊ ገቢያቸው 10
ፐርሰንት በሚበልጥ መልኩ ማሰባሰብ አይችሉም፡፡
አንቀጽ 13 ለመዋጮ ስብሰባ የተሰማራ ሰው ያሉበት ግዴታዎች
1. ማንኛውም በመዋጮ ሰብሳቢነት ላይ የተሰማራ ሰው የሚከተሉትን ማድረግ ይጠበቅበታል፡-
ሀ . የስብሰባውን ስራ የሰዎችን መብት በጠበቀ መልኩ እና በህግ አግባብ ማከናወን፤
ለ . የመሰብሰቡን ስራ በመልካም የሞራልና የስነ ምግባር ሁኔታ ማከናወን፤
ሐ . የመሰብሰብ ስልጣኑን የሚያሳይ መረጃ መያዝ እንዲሁም ከፖሊስ፣ መዋጮውን እየተጠየቀ ካለው ሰው ወይም
መረጃውን ማየት ከሚፈልግ ማንኛውም የሚመለከተው አካል ጥያቄ ሲቀርብለት ማሳየት፤
መ . መዋጮውን እየሰበሰበ ባለበት ማንኛውም ጊዜ የበጎ አድራጎት ድርጅቱን ወይም የማህበሩን ስምና አርማ የያዘ
የደረት ባጅ፤
ሠ . በመዋጮ ስብሰባው ወቅት ከመዋጮው ጋር በተያያዘ ከፍላጎት ውጪ አለመወትወት ወይም አለማስቸገር፤
ረ . በመኖሪያ

ቤት እና በተከለሉ ቦታዎች በሚደረግ የመዋጮ መሰብሰብ ሂደት ወቅት ወደ ውስጥ ለመግባት ፈቃድ
መጠየቅ እና እንዳይገባ ወይም ለቆ እንዲሄድ በተጠየቀ ጊዜ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መታዘዝ እንዲሁም
ከተደነገገው ሰዓት ውጭ በሰዎች መኖሪያዎች አለመሄድ፤
ሰ. ህዝባዊ መዋጮ ስራው በማይሰሩበት ሰዓት፣ በተጠናቀቀበት ጊዜ እና በተጠየቀ በማናቸውም ጊዜ መዋጮ

ለመሰብሰብ እንዲያስችለው የተሰጠውን ማንኛውንም መገልገያ መመለስ፤
ሸ . በተሰጠው የመሰብሰባ ስልጣን መሰረት የሰበሰበውን መዋጮ ህዝባዊ መዋጮውን ለማስረከብ በተዘረጋው
ሥርዓት መሰረት ለሚመለከተው አካል ማስረከብ፡፡ www.abyssinialaw.com

10 
 
ክፍል አራት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
አንቀፅ 14 ስለ ሪፖርት አቀራረብ
1. መዋጮውን የሚያስተባብረው አካል መዋጮው በተጠናቀቀ በ 3 ወር ውስጥ ከመዋጮው ጋር የተያያዘ ማንኛውንም
የገንዘብ እንቅስቃሴ እና የሃብት ሁኔታ የሚያሳይ ሪፖርት ለኤጀንሲው ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
2. ከላይ በንዑስ አንቀጽ አንድ የተጠቀሰው ሪፖርት ከገቢ እና ከወጪ ዝርዝር በተጨማሪ የመዋጮ አሰባሰቡን ሂደት
የሚያሳይ ሪፖርት ማያያዝ አለበት፡፡
3. መዋጮውን ያስተባበረው አካል ኤጀንሲው ከቀረበለት ሪፖርት ጋር ተያይዞ የሚጠይቃቸውን ማንኛውንም ጥያቄዎች
የመመለስ እንዲሁም መረጃዎችን ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
4. በዚህ አንቀፅ መሰረት ሪፖርት ሲያቀርብ ከማንኛውም አካል

ያገኘውን ከ ብር 5,000( አምስት ሺህ ) በላይ የሆነን
መዋጮ ከየት አካል እንደተገኘ በመግለፅ ማካተት ይገባዋል፡፡
5. ከላይ የተደነገገው ቢኖርም ኤጀንሲው አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ስለመዋጮው በሚመለከት ማንኛውም መረጃ
እንዲቀርብለት መጠየቅ ይችላል፡፡
አንቀፅ 15 መዋጮን በኮሚሽን ማከናዎን ስለመከልከሉ
ማንኛውም ህዝባዊ መዋጮ የሚያካሂድ በጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር በመዋጮው ከሚሰበሰበው ሃብት
መጠን ውስጥ የተወሰነውን ፐርሰንት ለመክፈል ወይም በሌላ በማናቸውም መንገድ ኮሚሽን ለመክፈል በመስማማት
ህዝባዊ መዋጮን ሊያካሂድ አይችልም፡፡

አንቀፅ 16 ሌሎች ግዴታዎች የተጠበቁ ስለመሆናቸው

በኤጀንሲው የህዝባዊ መዋጮ ፈቃድ መሰጠቱ ህዝባዊ መዋጮውን ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ በሌሎች ህጎች
የተመለከቱ ግዴታዎችን አያስቀርም፡፡
አንቀፅ 18 ስለ ቅጣት
1. ከህዝባዊ መዋጮ ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ ማናቸውም ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት በወንጀል ህጉ ድንጋጌዎች የሚሸፈኑ
መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም የበጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማህበር፡-
ሀ .በዚህ መመሪያ መሠረት ከኤጀንሲው ፈቃድ ሳያገኝ በህዝባዊ መዋጮ ማሰባሰብ ስራ ላይ ተሰማርቶ የተገኘ
እንደሆነ፤
ለ . በዚህ መመሪያ አንቀጽ 13 መሰረት ሪፖርት ያላቀረበ እንደሆነ፤
ሐ . በዚህ መመሪያ ክፍል ሶስት ስር የተቀመጠውን የመዋጮ አሰባሰብ ስርዓት ሳያከብር የቀረ እንደሆነ www.abyssinialaw.com

11 
 
እንደነገሩ ሁኔታና እንደጉዳዩ ክብደት ኤጀንሲው ከፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ቀጣይ የህዝብ መዋጮ ስብሰባ እቅዶችን
እስካልተወሰነ ጊዜ የማገድ እርምጃዎችን ሊወስድ ይችላል፡፡
2. በዚህ አንቀፅ የተደነገገው ቅጣት እንደተጠበቀ ሆኖ በአዋጁ አንቀጽ 91፣ 92 ፣ 93 ፣ 98 (3) እና 102 የተመለከቱ የስራ
መሪን ከሃላፊነት የማንሳት፣ ድርጅቱን ወይም ማህበሩን የማገድ፣ የማፍረስ እና ሌሎች ቅጣቶች እና እርምጃዎች
ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
አንቀፅ 19 ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው ሌሎች ህጎች
ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማንኛውም መመሪያና ልማዳዊ አሰራር ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡

አንቀፅ 20 መመሪያው የሚፀናበት ገዜ
ይህ መመሪያ በኤጀንሲው ፀድቆ ከወጣበት ከሐምሌ 9 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

አሊ ሲራጅ መሀመድ
የበጎ አደራጎት ድርጅቶችና ማኀበራት ኤጀንሲ
ዋና ዳይሬክተር www.abyssinialaw.com