Directive to Determine the Operational and Administrative Costs of Charities and Societies No. 2

For optimal readability, we highly recommend downloading the document PDF, which you can do below.

Document Information:


የበ ጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራትን
የዓላማ ማስፈፀሚያና አስተዳደራዊ
ወጪዎችን ለመወሰን የወጣ መመሪያ
ቁጥር 2/2003

ሐምሌ 2003
አዲስ አበባ
www.abyssinialaw.com

2

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራትን የዓላማ ማስፈፀሚያና አስተዳደራዊ
ወጪ
ዎችን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 2/2003

መግቢያ
የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት በጀ ታቸውን ለዓላማ ማስፈፀሚያና
አስተዳደራዊ ወጪ ሲመድቡ እንዴት ማስላት እንዳለባቸው የሚያሳይ የአፈጻጸም
መመሪያ በማውጣት ግልፅነትና ተጠያቂነት በማስፈን ሀብቱን ለተፈለገው አላማ
እንዲውል ማድረግ
አስፈላጊ በመሆኑ፤

የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ና ማህበራት ዓመታዊ የበጀት ዕቅዳቸው ን፤ የፕሮጄክት
ፕሮፖዛላቸውንና የበጀት አፈጻጸም ሪፖርታቸው ን ሲያቀርቡ ሕጉን የተከተለ መሆኑን
ለማረጋገጥ የሚያስችል መመሪያ አስፈላጊ በመሆኑ፤

ኤጀን ሲው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራትን የሂሳብ መግለጫና የኦዲት
ሪፖርት፤ የዘርፍ አስተዳዳሪዎች ደግሞ ፕሮጄክት ፕሮፖዛል በሚገመግሙ ወቅት
የበጀት ድልድሉ ና የተፈፀሙ ወጪዎች ለዓላማ ማስፈጸሚያና ለአስተዳደራዊ ስራዎች
መመደብ በሚገባው ስሌት አግባብ
መሆኑን ለማረጋገጥ፤

ኤጀንሲው የዓላማ ማስፈፀሚያና አስተዳደራዊ ወጪዎችን በተመለከተ ዝርዝር
የአፈጻጸም መመሪያ የማውጣት ስልጣን በደንብ ቁጥር 168/2001 አንቀጽ 2 0 ንዑ ስ
አንቀጽ 2 እና 3 በተደነገገው መሰረት የሚከተለው መመሪያ ወጥቷል፡፡

www.abyssinialaw.com

3

ምዕራፍ አንድ
ጠቅላላ ድንጋጌ
አንቀጽ 1. አውጪው አካል
የበ

ጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና
ማህበራትን ለመመዝገብና ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 621/2001 ለማስፈፀም
በወጣው የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 168/2001 አንቀጽ 34 በተሰጠው ሥልጣን
መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡
አንቀጽ 2.
አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራትን የዓላማ ማስፈፀሚያና አስተዳደራዊ
ወጪዎች
ለመወሰን የወጣ የአፈፃጸም መመሪያ ቁጥር 2/2003 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
አንቀጽ 3
. ትርጓሜ
በዚህ መመሪያ
ውስጥ የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሠጥ ካልሆነ በስተቀር፤
1. “
አዋጅ” ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራትን ለመመዝገብና
ለማስተዳደር የወጣ አዋጅ ቁጥር
621/2001 ነው፡፡
2. “
ደንብ” ማለት ስለበጐ አድራጐት ድርጅቶች እና ማህበራት ምዝገባና አስተዳደር
የወጣ
የሚንስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 168/2001 ነው፡፡
3. “
ኤጀንሲ” ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ነው፡፡
4. “
ቦርድ” ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ቦርድ ማለት ነው፡፡
5. “
ዋና ዳይሬክተር” ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ዋና
ዳይሬክተር ነው፡ ፡
6. “
አስተዳደራዊ ወጪ” ማለ ት ለደመወዝ፣ ለአበል፣ ለጥቅማ ጥቅም፣ ለእቃዎችና
ለአገልግሎቶች ግዢ፣ ለጉዞ እና ለመስተንግዶ የሚወጡ፣ለበጐ አድራጐት ድርጅቱ
ወይም
ማህበሩ አስተዳደራዊ ሥራዎች አስፈላጊ የሆኑ ወጪ ነው፡፡
7. “
ዓላማ ማስፈጸሚያ ወጪ” ማለት -የበጎ አድራጎት ደርጅቱ ወይም ማኀበሩ
የቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት ኀብረተሰቡን ተጠቃሚ ለሚያደርጉ ስራዎች ወይም
ተግባራት የሚወጣ ወጪ ነዉ፤

8. “
ስብስብ ” ማለት ለዚህ መመሪያ አፈፃፀም እንዲያግዝ ተቀራራቢ ወይም ተመሣሣይ
አላማ ያላቸው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማህበራት ወጥ የሆነ የአላማ www.abyssinialaw.com

4
ማስፈፀሚያ የወጪ አሰላል እንዲከተሉ የሚያስችል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች

ወይም ማህበራት
አደራጃጀት ነው፡፡
9. “
ጥቅማ ጥቅም” ማለት ማንኛውም የበጐ አድራጐት ድርጅት ወይ ም ማኀ በር
ለሠራተኞቹ በጥሬ ገንዘብ ወይም በአይነት የሚሰጥ
ክፍያ ወይም አገልግሎት ሆኖ
ፕሮ ቪደንት ፈንድ፣ ቦነስ፣ ካሣ፣ የስራ ስንብት ክፍያ ፣እና ዋስትና የመሣሠሉትን
ያጠቃልላል ፡፡
10. የሂሳብ መግለጫ ማለት – ማንኛውም የበጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማ
ኀበር
ወይም የበጎ አድራጎት ኮሚቴ በበጀት አመቱ መጨረሻ ላይ ለኤጀንሲው
የሚያቀርበው የሀብትና እዳ ሚዛን ትንተና በዓመቱ የሰበሰበውን የገቢ መጠንና
ምንጩን እንዲሁም የወጪዎችን ዝርዝር ተቀባይነት ያለው የሂሳብ አሰራርን
በመከተል
ሠርቶ የሚያቀርበው ሰነድ ነው፡፡
11. የኦዲት ሪፖርት ማለት –
በኦዲተር ተመርምሮ አስተያየት የተሰጠበት የበጐ
አድራጐት ድርጅቱን ወይም ማኀ
በሩን ወይም የበጎ አድራጎት ኮሚቴዉን የሀብትና
እዳ ሚዛን ትንተና በዓመቱ
የሰበሰበውን የገቢ መጠንና ምንጩን እንዲሁም
የወጪዎችን ዝርዝር ተቀባይነት ባለው የሂሳብ አሰራርን በመከተል ሠርቶ
የሚያቀርበው
ሰነድ ነው፡፡
12 . በአዋጅና በማስፈፀሚያ ደንቡ ላይ የተቀመ ጡት ሌሎች ትርጓሜዎች በዚህ
መመሪያ ላይ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
13 በዚህ መመሪያ ዉስጥ በወንድ ፆታ የተደነገገው የሴትንም ፆታ ያካትታል፡፡
አንቀጽ 4.
የተፈጻሚነት ወሰን
ይህ መመሪያ
ሀ. ከአንድ በላይ በሆኑ ክልሎች በሚሰሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማኀበራት
ወይም የአባላት ጥንቅራቸዉ ከአንድ ክልል በላይ በሆኑ ማኀበራት፤
ለ. በአን

ድ ክልል ብቻ የሚሰሩ ቢሆንም በዉጭ አገር በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና
በኢትዮጵ ያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኀበራት፤
ሐ. በአዲ

ስ አበባ ወይም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በሚሰሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና
ማኀበራት፤
መ. በአዋጁ አንቀጽ 48 መሰረት በኤጀንሲው ቀርበው የማጽደቅ ውሳኔ የተሰጣቸው የበጎ
አድራጎት ኮሚቴዎች
ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
አንቀጽ 5. የመመሪያው ዓላማ www.abyssinialaw.com

5
የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት በጀታቸውን ለዓላማ ማስፈፀሚያና
አስተዳደራዊ ወጪዎች ሲመድቡ ግልፅነትና
ተጠያቂነት ባለበት ሁኔታ ተፈፅሞ ሀብቱ
ለተፈለገ የልማት ዓላማ መዋል እንዲችል ለማድረግና አፈፃፀሙም የሕዝቡ የላቀ
ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ አግባብ መሆኑን ለመከታተልና ለመቆጣጠር ነው ፡፡

ምዕራፍ ሁለት
የበጐ አድራጐት ድ ርጅቶች ወይም
ማኀበራት ስብስብና (Cluster) የወጪዎች
ዝርዝር
አንቀጽ
6. ስብስብ
የበ
ጐ አድራጐት ድርጅቶች በአዋጁ አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ 2 (ሀ –
ኘ) ፤እና አንቀጽ 15
ንዑ ስ አንቀጽ 3 በሚፈጥሩት አደረጃጀትና የሚሰማሩባቸውን አላማዎች መሠረት በማድረግ
ተመሣሣይና ተቀራራቢነት አላማ ያላቸውን በመለየት ለዓላማ ማስፈፀሚያ በጀት ለማስላት
በሚያመች መልኩ ከዚህ በታች በተመለከቱት ስብስቦች እንዲደራጁ የተደረገ ሲሆን
ማኀ
በራት ግን በይዘታቸዉ የተለያዩ ቢሆኑም ዓላማቸዉ የአባሎቻቸዉን ጥቅም ማስጠበቅ
ጋር የተያያዘ በመሆኑ ስብስብ ሳያስፈልጋቸዉ በተለየ ሁኔታ ለብቻቸዉ ይታያሉ ፤
ስብስቦቹም፡ –

1 . በሴቶችና ህፃ ናት ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤

2 . በ ኤች .አይ ቪ.ኤድስ መከላከል እና ጤና ማስፋፋት ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት
ድርጅቶች፤

3 . በግብርና፣ ምግብ ዋስትና፣ህይወት ማዳንና አካባቢ ጥበቃ ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ
አድራጎት ድርጅቶች፤

4 . በትምህርት ማስፋፋት ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤

5 . በአካ ል ጉዳተኞች፣ ጎዳና ተዳዳሪዎችና አረጋዊያን በመደገፍ ስራ የሚንቀሳቀሱ የበጎ
አድራጎት ድርጅቶች፤

6 . በባህል፣ ቅርስ፣ ወጣቶችና ስፖርት ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤

7 . በሰብዓዊና ዴሞክራሲያው መብቶች ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤

8 . በግጭት አፈታት፣ የፍትህና የህግ አፈጻጸም ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት
ድርጅቶች፤

9 . በአቅ ም ግንባታ፤ምርምርና ጥናት ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤

10. በስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች
ናቸው :: www.abyssinialaw.com

6

አንቀጽ
7. ስብስቦቹን ስለ ማሻሻል
የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማኀበራት በሚፈጥሩት አደረጃጀትና
ከሚሰማሩባቸው አላማዎች አንጻር በዚህ መመሪያ አንቀጽ 6 ላይ የተዘረዘሩት
ስብስቦች
ቢኖሩም ኤጀንሲው አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሊያሻሽለዉ ይችላል ።
አንቀጽ 8. የአስተዳደራዊ ወጪዎች ዝርዝር
1.

በጎ አድራጎት ድርጅቶች

በአዋጁ አንቀፅ 2 ንዑ ስ አንቀጽ 14 የተደነገገው የአስተዳደራዊ ወጪ ዎች ትርጉም
እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅት ከዚህ በታች የተመለከቱትን
ወጪዎች በአስተዳደራዊ ወጪ ስር ሊይዝ ይገባዋል፡፡
ሀ . ለተለያዩ የቢሮ ስራዎች (ለአስተዳደራዊ ስራዎች) ለሚው ሉ አገልግሎቶችና እቃዎች
የሚፈፀሙ ክፍያዎ ች፡-
አላቂ እቃዎች ግዢ፣ ለቋሚ እቃዎች ግዢ፤ ጥገናና እድሳት
የሚደረጉ ወጪዎች፣ለፓርኪንግ የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ለኦዲት አገልግሎት፣
ማስታወቂያ፣ለባንክ አገልግሎት፣ መብራት፣ ስልክ፣ ፋክስ፣ ውሃ፣የህትመት ወጪዎች ፣
ፖስታ፣የቢሮ ኪራይ፣ ታክስ፣ ኢንተርኔት፣የወለድ ወጪ (Interest Expense)፤
የአባልነት መዋጮ፤ለተሸከርካሪዎች ግዢ፤ጥገና፤የነዳጅና ዘ ይት እንዲሁም ለዋስትና
የሚደረጉ ወጪዎች፣ የቅጣት ክፍያዎች፣ የማማከር አገልግሎት ክፍያ
(Consultancy fee)፣የጥብቅና አገልግሎት ክፍያ፣ለቅጥር የሚወጡ ወጪዎች፣
ክትትልና ቁጥጥር ለማካሄድ የሚወጡ ወጪዎች፣ የተለያዩ ስብሰባዎች ለማካሄድ
የሚደረጉ ወጪዎች፤ እቅድና ሪፖርት ዝግጅት፣የምዝገባ ወጪ፤ለተጠቃሚዎች
ከሚከፈለው ውሎ አበልና የስልጠና ማቴሪያል ለማዘጋጀት ከሚወጣው ወጪ ውጭ
ያለው ማንኛውም የስልጠና ወጪ እና ውሎ አበል ፤ለመስተንግዶና ለጉዞ
የሚወጡ ወጪዎች
ለ. ከሥራው ጋር ወይም ዓላማውን
ለማሳካት አገልግሎት ለሚሰጡ የሥራ መሪዎች እና
ለደ ጋፊ
ሰጪ ሠራተኞች የሚከፈል ደመወዝ ፣ አበልና ጥቅማ ጥቅም ሆኖ
የሚከተሉትን ሠራተኞች ያጠቃልላል፡፡ ማንኛውም የሥራ መሪ፣ ሂሳብ ሹም፤
አስተዳደርና ፋይናንስ፣ ንብረት ክፍል፣የትራንስፖርት ስምርት፣ ገ/ያዥ፣ ኦዲተር፣
ጥበቃ፣ ሹፌር፣ የፕሮግራምና የፕሮጀክት ዳይሬክተር(አስተባባሪ)፤ የሰው ሀብት www.abyssinialaw.com

7
አስተዳደር፣ ተላላኪ፣ ጽዳት ሠራተኛ፣አትክልኛ፤
ፀኀፊ እና የመሳሰሉት
ሰራተኞች
ሐ. ማንኛውም የቢሮ ግንባታና ጥገና፤ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ወጪ፤
እንዲሁም የአጥር ግንባታ ወጪ ፡፡
2. ማህበራት

በዚሁ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 ከተዘረዘሩት የበጐ አድራጎት ድርጅቶች አስተዳደራዊ
ወጭዎች ውስጥ የማህበሩን ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ የሚወጣ ወጪ የአዳራሽ ኪራይ፣
ሪፖርት ዝግጅት ወጪ፤እንዲሁም ለአጋር ማህበራት ከሚከፈል የአባልነት መዋጮ
በስተቀር ሌሎች
አስተዳደራዊ ወጪዎች ለማኀበራትም ተፈፃሚ ይ ሆናሉ፡፡

3 በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (1) እና (2) የተዘረዘሩት ወጪዎች እንደተጠበቁ ሆነዉ ኤጀንሲዉ
አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሊያሻሽለዉ ይችላል፡፡
አንቀጽ
9. የዓላ ማ ማስፈፀሚያ ወጪዎች ዝርዝር
የዓላማ ማስፈፀሚያ ወጪዎች የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በሚፈጥሩት አደረጃጀትና
የሚሰማሩባቸውን ዓላማዎች መሠረት በማድረግ በዚህ መመሪያ አንቀጽ 6
ስር
በተቀመጠው አግባብ ለየስብስቡ ተለይቶ ከዚህ መመሪያ ጋር በተያያዘው አባሪ 1
እንዲሁም ማኀበራትን በተመለከተ በአባሪ 2 ላይ የተዘረዘረ ቢሆንም ከዚህ በታች
የተገለጹት የዓላማ ማስፈጸሚያ ወጪዎች ተብለው
ይያዛሉ።
ሀ. ለተጠቃሚዎች የሚደረጉ የተለያዩ ድጋፎች፡ የአልባሳት፤ ለተጠቃሚዎች የሚውል
የጽህፈት መሣሪያ ግዥ፣የገንዘብ ድጋፍ፤ የምግብ አቅርቦት፣የማምረቻ መሳሪያዎች እና
ጥሬ ዕቃ አቅርቦት ግዢ፤ ኬሚካሎች ግዢ፣የመድሐኒት፣የህክምና ወጪዎች ፣
የማምረቻ መሣሪያዎች ድጋፍ፤መኖ አቅርቦት፤ ለእንስሳት ግዥ፤ የተሻለ ቴክኖሎጂ
አቅርቦት የሚወጣ ወጪ፣ ለምርቶቻቸው መሸጫ ቦታ ግንባታ የሚወጣ ወጪ ሌሎች
ቁሳዊ ድጋፎች፤
ለ . ከዓላማው ጋር ቀጥታ ተያያዥ ለሆኑ ግንባታዎች የሚወጡ ድጋፎች፡ ለግንባታ
የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎችና የግንባታ መሳሪያዎች ግዢና ለዕድሳት የሚደረጉ
ወጪዎች፣ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት የሚውል የው ሀ፤የመብራት እና የመሳሰሉትን
አገልግሎቶች አቅርቦት ፡፡

ሐ . ለተጠቃሚዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ ለሚሰሩ ስራዎች የሚደረግ ወጪ ፡- ( ድራማ፣
የህትመት ውጤቶች፣ የአየር ሰዓት ክፍያ ፣ የሰልጣኞች አበል፣ የስልጠና ማቴሪያል
ዝግጅት ወጪ)፤ www.abyssinialaw.com

8
መ .
ከአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች ጋር በቀጥታ ለሚገናኙ ተግባራት የሚወጡ
ወጪዎች፡
ሠ.ፓርኮችን ከማልማትና ከመጠበቅ
ጋር በቀጥታ ለሚገናኙ ተግባራት የሚወጡ

ጪዎች

ረ. የበጎ አድራጎት ደርጅቱ ወይም ማሀበሩ የቋቋመበትን አላማ ከማሳካት አንጻር
ለተጠቃሚዎች ከሚሰጡ አገልግሎቶች ጋር በቀጥታ ተያያዥ የሆኑ ስራዎች ላይ
ለተሰማሩ ሰራተኞች የሚከፈል ደመወዝ፤ ለትምህርት ቤቱ መምህራን፣ በጤና
ተቋሙ ለጤና ባለሙያዎች፣ ለግብርና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣ ለመጠጥ ውሃ
ቁፋሮ ማሽን ኦኘሬተር፣ ለህጻናት ሞግዚቶች ወይም ተንከባካቢዎች እና
ለመሳሰሉት፡፡

አንቀጽ 10. ስለሕብረት ወጪዎች

1 የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ሕብረቶች በአዋጁ አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ 3
እና አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ 4 መሠ ረት የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት
ሥራዎቻቸውን ለማስተባበር፣ ለመደገፍ እና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ለማካሄድ
የሚ ያቋቋሙት ሆነው የገቢ ምንጫቸውም
፡-

ሀ. ከሕህብረቱ አባል ድርጅቶች የሚከፈል ዓመታዊ የአባልነት መዋጮ እና

ለ. ሕብረቶቹ በአባል ድርጅቶቹ ስም ለልማት ከሚያሰባስቡት ሀብት አባል ድርጅቶቹ
ለአስተዳደራዊ ወጪ ከሚጠቀሙበት ከ30 ከመቶ ድርሻቸው ላይ ጠቅላላ ጉባዔያቸው

በሚወስነው
መጠን መሠረት የሚገኝ ገቢ ይሆናል፡፡

2 . የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኀበራት ሕብረቶች ፈፃሚዎች ባለመሆናቸው
አስተዳደራዊ ወጪ
እንጂ የዓላማ ማስፈፀሚያ ወጪ አይኖራቸዉም፣
3 የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 እንደተጠበቀ ሆኖ ሕብረቶቹ የሚሰባስቡት ሀብትና
ወጪያቸው ጠቅላላ ጉባኤ በሚያጸድቀው
ዓመታዊ ዕቅድ መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

አንቀጽ 11. አስፈላጊውን የሰው ሀይል፣ የደመወዝ እና የማቴርያል መጠን ስለ መኖር

ሀ . ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅ ት ወይም ማ ኀበር ሰራተኛ ሲቀጥር የበጎ አድራጎት
ድርጅ ቱ ወይም ማህበሩ እያከናወነ ካለው ስራ አንጻር የግድ የሚያስፈልጉ
ሰራተኞችንና ማቴሪያል የተመጣጠነ የሰው ሀይልና ሎጂስቲካዊ አቅርቦት ብቻ
መሆን አለበት።

ለ. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ሀ የተገለጸዉ እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛዉም የበጎ
አድራጎት ድርጅ ት ወይም ማኀ
በር ለሚቀጥረዉ ሰራተኛ የሚከፍለው የደመወዝ
መጠን (scale) ከአገሪቷ ኢኮኖሚ ጋር ተመጣጣኝና ያልተጋነነ መሆን
ይኖርበታል፡፡
ሐ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ሀ ስር የተጠቀሰው ቢኖርም ይህን ን መመሪያ በማክበርና
እንዲከበር የተንቀሳቀሱ ወገኖችን ለመጉዳት የሚንቀሳቀስ በጎ አድራጎት ድርጅት
ወይም ማህበር ወይም የስራ መሪ መኖሩ ከተረጋገጠ ኤጀንሲው በበጎ አድራጎት www.abyssinialaw.com

9
ድርጅቱ ወይም ማኀበሩ ወይም የስራ መሪ ላይ የሚ
ሰጠው
ውሳኔ እንዲከብድ
ሊያደርገው ይችላል፡፡

ክፍል ሦስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

አንቀጽ 1 2. የህግ ተጠያቂነት
ሀ.
የዚህን መመሪያ ድንጋጌዎች የጣሰ ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም
ማህበር በአዋጁ አንቀጽ 102 በተደነገጉት ቅጣቶች መቀጣቱ እንዳለ ሆኖ ኤጀንሲዉ
እንደ አስፈላጊነቱ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ
እስከስረዛ መሄድ የሚችል እርምጃ
ይወስዳል፡፡
ለ. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ሀ የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ከጠቅላላ ዓመታዊ
በጀቱ ከ80 በመቶ በላይ ለዓላማው ማስፈጸሚያ ለሚያውል ወይም የላቀ የስራ አፈጻጸም
ላሳየ በጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማኀ
በር ኤጀንሲው የተለያዩ ማበረታቻዎችን
ሊያደርግ ይችላል፡፡
አንቀጽ 1 3
ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው መመሪያዎች

ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማንኛውም መመሪያ ወይም ባህላዊ አሰራር
ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡
አንቀጽ
14. መመሪያዎች ስለሚሻሻል በት ሁኔታ
ኤጀንሲው
ይህንን መመሪያ ተግባራዊ ሲያደርግ የሚከሰቱ ክፍተቶችን ለመሙላት
አዋጁን

ደንቡን የሚጠቀም ሲሆን በሂደት ከሚያገኛቸው ልምዶች በማንኛውም ጊዜ
ሊያሻሽለው
ይችላል፡፡
አንቀጽ .15 መመሪያው
የሚጸናበት ጊዜ
ይህ መመሪያ በቦርዱ ፀድቆ ከወጣበት ከሐምሌ 9 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ
ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ ሐምሌ 2003 ዓ.ም
ዓሊ ሲ ራጅ www.abyssinialaw.com

10
የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ

ዋና ዳይሬክተር

አባሪ 1
ለበጎ አድራጎት ድርጅት ስብስቦች የዓላማ ማስፈጸሚያ ወጪዎች ዝርዝር

በዚህ መመሪያ አንቀጽ 5 ለተዘረዘሩት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ስብስቦች የዓላማ
ማስፈፀሚያ ወጪዎች የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡፡
7.1 በህፃናትና ሴቶች ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጐ አድራጐት ድርጅቶች

ሀ. የትምህርት አገልግሎትን ለማስፋፋት የሚወጡ ወጪዎች፡ – ለትምህርት ቤት ወይም
ለስልጠና ማዕከላት ግንባታ ለሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎችና ግንባታ መሳሪያዎች ግዢና
ለዕድሳት የሚደረጉ ወጪዎች፣ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችና ሌሎች ቋ ሚ
ዕቃዎች ግዥ፣ለህጻናቱ ወይም ለሴቶቹ ዶርሚተሪና መጸዳጃ ቤት ግንባታ
ለሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎችና ግንባታ መሳሪያዎች ግዢና ዕድሳት ወጪዎ፡፡

ለ. ጤና አገልግሎት ማስፋፋትን መሰረት ያደረገ ወጪዎች፡ – የጤና ተቋማን
ለመገንባትና ዕድሳት ለማካሄድ የሚደረጉ የጥሬ እቃዎችም ሆነ የግንባታ
መሳሪያዎች ግዢና ለዕድሳት የሚደረጉ ወጪዎች፣ ስነ-
ተዋልዶና የቤተሰብ ምጣኔ
አገልግሎት ወጪዎች፣ ለህፃናት ንጽህና አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶች ግዥ፣
የህክምና መሣሪያዎች፣ አገልግሎቶች እና መድሃኒት ግዢ፡፡

ሐ. ለህፃናቱ ወይም ለሴቶች የሚደረጉ የተለያዩ ድጋፎች፣ (የአልባሳት፤ለተጠቃሚዎች
የሚውል የጽህፈት መሣሪያ ግዥ፤ለመኖሪያ ቤት ግንባታ ለሚያገለግሉ ጥሬ
ዕቃዎችና ግንባታ መሳሪያዎች ግዢና ለዕድሳት የሚደረጉ ወጪዎች፣የገንዘብ
ድጋፍ፤የምግብ አቅርቦት፣የማምረቻ መሳሪያዎች እና ጥሬ ዕቃ አቅርቦት ግዢ፤
ሌሎች ቁሳዊ ድጋፎች)

መ . ለተጠቃሚዎች የ ግንዛቤ ማስጨበጫ ለሚሰሩ ስራዎች የሚደረግ ወጪ። ( ድራማ፣
የህትመት ዉጤቶች፤የአየር
ሰዓት ክፍያ ) ፤ www.abyssinialaw.com

11

ሠ. በኤች.አይ.ቪ.ኤድስ መከላከል በጤና አጠባበቅ ዙሪያ እንዲሁም ጐጂ ልማዳዊ
ድርጊቶችን ለማስቀረት ለተጠቃሚዎች በሚደረጉ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ
ሥልጠናዎች የሚወጣ ወጪ (ለተጠቃሚዎች የሚከፈል የውሎ አበልና የስልጠና
ማቴሪያሎች ግዥ )፡፡

ረ. ለሞግዚቶች፣ በጤና ተቋሙ ለጤና ባለሙዎች አንዲሁም ህጻናቱን ለሚያስተምሩ
መምህራን የሚከፈል ደመወዝ ፡፡

7.2 በጤናና ኤች.አይ.ቪ.ኤድስ ዙሪያ ለሚንቀሳቀሱ

ሀ. ለቫይረሱ ተጠቂዎችም ሆነ ተጋላጭ ወገኖች የሚደረግ ማንኛውም የምክርና የደም
ምርመራ አገልግሎት ወጪ፣ የኮንዶም ሥርጭት፣ የመድኃኒት ግዥና አቅርቦት፣
የምግብና የአልባሳት ወጪ፣ የገንዘብ ድጋፍ፣ እራሳቸውን እንዲችሉ ታስቦ የሚሰጥ
የሙያ ሥልጠና፣ የማምረቻ መሣሪያዎች ድጋፍ፡፡
ለ. ጤና አገልግሎት ማስፋፋትን መሰረት ያደረገ ወጪዎች፡ –
የጤና ተቋማን ለመገንባትና
ዕድሳት ለማካሄድ የሚደረጉ የጥሬ እቃዎችም ሆነ የግንባታ መሳሪያዎች ግዢና
ለዕድሳት የሚደረጉ ወጪዎች፣ ስነ-
ተዋልዶና የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ወጪዎች፣
ለህፃናት ንጽህና አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶች ግዥ፣የህክምና መሣሪያዎች፣
አገልግሎቶች እና መድሃኒት ግዢ፡፡

ሐ. በኤች.አይ.ቪ.ኤድስ መከላከልም ሆነ በጤና አጠባበቅ ዙሪያ ያተኮሩ ለተጠቃሚዎች
ለሚሰጡ
የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎች (ለተጠቃሚዎች የሚከፈል ውሎ አበል፣
የስልጠና ማቴሪያሎች ግዥ)፡፡

መ. ለወባና ውሀ ወለድ እንዲሁም ሌሎች ተላላፊ እና ተዛማች በሽታዎችን ለመከላከል ለሚሠሩ የአቅርቦትና የመከላከል ሥራዎችና ለክትባት የተደረገ ወጪ፡፡

ሠ.ለግን ዛቤ ማስጨበጫ ለሚሰሩት ስራዎች የሚ ደረግ ወጪ። – (ድራማ፣የህትመት
ዉጤቶች፤የአየር
ሰዓት ክፍያ ) ፤

ረ. ለሞግዚቶች እና ፣ለጤና ባለሙያዎች የሚከፈል ደመወዝ ፡፡

7.3 ግብርና፣ ምግብ ዋስትና፣ህይወት ማዳንና አካባቢ ጥበቃ ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ
www.abyssinialaw.com

12
ሀ. ምርትን ለማሳደግና ለተሻሻለ ቴክኖሎጂ አቅርቦት የሚደረግ ወጪ።
-ምርጥ ዘር
ብዜትና ስርጭት፣ ፀረ –
ተባይ፣ ፀረ አረም፣ የግብርና መሣሪያዎች፣ ሀይል ቆጣቢ
ምድጃ፣ ሶላርና ለባዮጋዝ ግንባታ ወጪ፣ ማዳበሪያ፣ ፕላስቲክ ባግ ግዢ፣ለመሰረተ
ልማት ግንባታ የሚወጡ ወጪዎችና ለገጠር ብድር አገልግሎቶች የሚሰጥ
የገንዘብና ቁሳዊ ድጋፍ እንዲሁም የመጋዝን ኪራይ ወይም ግንባታ ፡፡
ለ. ለአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች የሚወጡ ወጪዎች፡ ችግኝ ማፍላት፣ ስርጭትና ተከል፣ እርከን ሥራ፣ ዎተር ሼድ ማኔጅመንት፣ ለአነስተኛ መስኖ ግንባታና ጥገና
የሚደረግ ወጪ ፡፡
ሐ. ለአርሶ አደሩም ሆነ ለአርብቶ አደሩ በገቢ ማስገኛ ሥራዎች፣ በአካባቢ ጥበቃ፡ በምግብ ዋስትናና በግብርና ልማት ዙሪያ ለሚሠጡ ስልጠናዎች የሚወጣ ወጪ፤
(ለተጠቃሚዎች የሚከፈል የውሎ አበል፣ የስልጠና ማቴሪያሎች ወጪ፣ የስልጠና
ማእከላት ግንባታ ወጪ) እና ሌሎች ድጋፎች ፡፡
መ. የአካባቢን ብክለት ለመቀነስ የሚከናወኑ የምርምር ዉጤቶችን ተግባር ላይ
ለማዋል
የሚወጣ ወጪ ፡፡
ሠ. የእንስሳትን ደህንነትና ጤንነት ለመጠበቅ የሚደረግ ግንባታ፣ የህክምና መድኃኒ ት
አቅርቦትና አገልግሎት፣ መኖ አቅርቦት፤ ለእንስሳት ግዥ፣ የዱር እንሰሳትን
ደህንነት፣ ፓርኮችን ለማልማትና ለመጠበቅ የሚረዱ ቁሳዊና የገንዘብ ወጪ ፡፡
ረ. ህይወትን ለማዳን የሚወጣ ወጪ፡ –
የድንኳን ግዢ፣ መጠለያ፣ የምግብ አቅርቦት፣
ህይወትን ለማዳን የሚያስፈልጉ ቦቲዎችና ጀልባዎች፣ ነዳጅና መኪና ኪራይ፣
መድሀኒት ግዥና
አቅርቦት ፡፡

ሰ . ደመወዝ ለግብርና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የሚከፈል ደመወዝ ፡፡

7.4 በትምህርት ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ

ሀ. የትምህርት አገልግሎትን ለማስፋፋት የሚወጡ ወጪዎች፡ – ለትምህርት ቤት ወይም
ለስልጠና ማዕከላት ግንባታ ለሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎችና ግንባታ መሳሪያዎች
ግዢና ለዕድሳት የሚደረጉ ወጪዎች፣የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችና ሌሎች
ቋሚ ዕቃዎች ግዥ፣ለህጻናቱ ወይም ለሴቶቹ ዶርሚተሪና መጸዳጃ ቤት ግንባታ
ለሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎችና ግንባታ መሳሪያዎች ግዢና ዕድሳት
ወጪዎች፡፡

ለ . ለተማሪዎች የሚደረጉ የተለያዩ ድጋፎች፤(የአልባሳት፤ለተጠቃሚዎች የሚውል
የጽህፈት መሣሪያ ግዥ፤የህክምና አገልግሎት ወጪ፣የገንዘብ ድጋፍ፤የምግብ
አቅርቦት፣ የሙያና የቴክኒክ ስልጠናዎችና ሌሎች ቁሳዊ ድጋፎች)፤ www.abyssinialaw.com

13

ሐ . ለት /ቤቱ መምህራን የሚከፈል ደመወዝ፤
7.5 አካል ጉዳተኞች፣ ጎዳና ተዳዳሪዎችና አረጋዊያን ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ

ሀ. እንደየአግባብነቱ ለአካል ጉዳተኞችም ሆነ ለአረጋዊያን የሚደረጉ የተለያዩ
ድጋ
ፎች፡ –
የተለያዩ አጋዥ መሳሪያዎች ድጋፍ( ብሬይል፣ ዊልቸር፣ ትራይ ሳይክል፣
መነጽር
እና የመሳሰሉት)፤ የአልባሳት፣ የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ ፣ የገንዘብ
ድጋፍ፣
የምግብና መጠለያ፣ የህክምና ወጪዎች ፣ የማምረቻ መሣሪያዎች ድጋፍ፤
የጥሬ ዕቃዎች ግዥ፣ ለምርቶቻቸው መሸጫ ቦታ ግንባታ የሚወጣ ወጪ ፡፡

ለ. ለመሠ ረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት ግንባታ የሚወጣ ወጪ ( ለመጠጥ ውሃ
አቅርቦት፣ ለመጸዳጃ ቤት፤ለመኖሪያ ቤት፤
ለመብራት አቅርቦት፡፡

ሐ. የአካል ጉዳተኞችን፤አረጋዊያንና ጎዳና ተዳዳሪዎችን በተመለከተ ለሚታተሙ
የህትመት ውጤቶች የሚደረጉ ወጪዎችና ለሚዲያ አስተምህሮት የሚወጡ
ወጪዎች፤

መ . እራሳቸውን እንዲችሉ የሚደረግ ሙያዊ ስልጠና( ለተጠቃሚዎች የሚከፈል አበል፤
የስልጠና ማቴሪያል ዝግጅት ወጪ) ፡፡

ሠ. ወይም ለሞግዚቶች የሚከፈል ደመወዝ ፡፡
7.6
ለጥበብ፣ ባህል፣ ቅርስ ወጣቶችና ስፖርት ዙሪያ የሚሰሩ

ሀ. ለስፖርተኞችና ለዘርፉ ተብሎ የሚካሄድ የስፖርት ትጥቆችንና የስፖርት ቁሳቁሶች ግዥ፣
የገንዘብ ድጋፍና ሌሎች ቁሳዊ ድጋፎች ፡፡
ለ. በውድድርም ሆነ በልምምድ ለስፖርተኞች የህክምና ወጪ፣ ለአሸናፊዎች የሚሰጥ
የሽልማት ወጪ ፡፡
ሐ. የስፖርትና የወጣት ማዕከላት፣ የቤተ መጽሐፍት ግንባታና ጥገና፤የውስጥ ቁሳቁስ ለማደራጀት የሚወጣ ወጪ፣ ስነ –
ጥበብና ኪነ-ጥበብ እንዲስፋፉ የተደረገ የቁሳቁስ
ድጋፍ
መ . ስራ አጥ ወጣቶችና ሴቶችን የሙያ ስልጠና የሚሰጡ ተቋማት ለመገንባትና
የው ስጥ ቁሳቁስ ለማደራጀት የሚደረግ ወጪ፣የማምረቻና መሸጫ ቦታ ዝግጅት
ወጪ፣የ
ገንዘብና ሌሎች ቁሳዊ ድጋፎች፣የስልጠና ማቴሪያል ዝግጅት ግብዓት
የሚወጣ ወጪ፤
ሠ. ቅርሶችና አገር በቀል ባህሎች አንዲጠበቁ ለማድረግ የሚካሄድ የሙዚየም
ግንባታ፤ ተፈላጊ ቅርሶች መሠብሰብ፣እና ባህልና ቅርስን፣ ቱሪዝም እንዲስፋፋና
መዳረሻዎችን የማስተዋወቅ ሥራ ወጪ፡ –
www.abyssinialaw.com

14
ረ. የስፖርተኞች፣
የስፖርት አሰልጣኞች፤ ለስፖርተኞች ወጌሻዎችና ሀኪሞች የሚከፈል
ደመወዝ፤

7.7 ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ

ሀ. በሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ዙሪያ በ ጐጂ ባህል ቅነሳ፣ በሴቶችና ህፃናት
መብት፣ ሕገ መንግሥት፣ ምርጫንና መልካም አስተዳደርን በሚመለከት ለሚሰጥ
ስልጠና የሚወጣ ወጪ (ለተጠቃሚዎች የሚከፈል አበል፣ ለስልጠና ማቴሪያሎች
ዝግጅት)፤

ለ. ሰብ ዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በሚመለከት የሚወጣ የህትመቶች ወጪ፤

ሐ. ሰብአዊ መብት ጥሰቶችን (ተጐጂዎችን) ለመርዳት የሚወጣ የቁሳቁስ ወጪ፤

መ . ምርጫን ለመከታተልና ለመታዘብ የሚወጣ ወጪ(የታዛቢዎች አበል፣
ትራንስፖርት ወጪ፣ ለስራው አጋዥ የሚሆን የስልጠናና ማቴሪያሎች ዝግጅት
የሚወጣ ወጪ)፣

ሠ . የሚዲያ አየርጊዜ ክፍያ::
7.8
በግጭት አፈታትና የሕግ አፈጻጸም አገልግሎት ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ

ሀ. የግጭት አፈታትን በተመለከተ ለተጠቃሚው የሚሰጥ ስልጠና የሚወጣ ወጪ
(
የስልጠና ማቴሪያሎች ዝግጅት፣ የሰልጣየኞች ውሎ አበል ) ፤

ለ. ማህበረሰብ አቀፍ (community based) ለሆኑ እንደ እድርና የሀገር ሸማግሌዎች
ለተለያዩ አደረጃጀት በግጭት አፈታትና ዕርቅ ዙሪያ የሚደረጉ ቁሳዊና የገንዘብ
ድጋፍ፣ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች፣እና ባህላዊ የግጭት አፈታትን
ለማበረታታት የሚወጣ ወጪ፤

ሐ. በህግ አፈጻጸም ዙሪያ ለተጠቃሚዎች የሚሰጡ ሥልጠናዎች ወጪ(
ለተጠቃሚዎች አበል፣ የስልጠና ማቴሪያሎች ዝግጅት፡፡

7.9. በአቅም ግንባታ፤ምርምርና ጥናት ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች

ሀ. ለተጠቃሚዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና (ለተጠቃሚዎች የሚከፈል አበል፣
ለስልጠና ማኑዋሎች ዝግጅት የተደረገ
ወጪ፤

ለ. ለተጠቃሚዎች የሚሰጥ ማንኛዉም ቁሳዊና የገንዘብ ድጋፎች ያካትታል፤

ሐ . በምርምር ላይ የተሰማራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከሆነ የምርምር ዉጤቶች ለሆኑ
ተግባራት
የሚወጣ ወጪ፤

7.10. በስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ www.abyssinialaw.com

15
1.
ስደተኞችን ለማቋቋም የሚደረጉ የተለያዩ ድጋፎች፡ –
የምግብ፣የገንዘብና ሌሎች
ቁሳዊ ድጋፎች፣ የአልባሳት፣ የመኖሪያ ካምኘ ግንባታ ለሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎችና
ግንባታ መሳሪያዎች ግዢና ለዕድሳት የሚደረጉ ወጪዎች ለድንኳን ግዥዎች
የሚወጡ ወጪዎች፤የግንባታና የጥገና ወጪ፤
2. ለትምህርት እና ለጤና ተቋማት ግንባታ ለሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎችና ግንባታ
መሳሪያዎች ግዢና ለዕድሳት የሚደረጉ ወጪዎች፤

3. የተለያዩ መሰረተ ልማትን ለማስፋፋት ለሚደረጉ ግንባታዎች የሚወጣ ወጪ፡ –
(ለመንገድ ግንባታ፣ የመጸዳጃ ቤት ግንባታ፣የወፍጮ ቤት ግንባታ፣ የመብራት
አቀርቦት፣ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት ማከማቻና ማሰራጫ፣ ለምንጭ ማጐልበት )

4. የትምህርት ቁሳቁሶች ግዢ፣ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችና ኬሚካሎች ግዢ፣
የመድሐኒት፣ የህክምና አገልግሎት ግዥ፤

አባሪ 2
ማህበራትን በሚመለከት አላማ ማስፈፀሚያ ወጪዎች

ማህበራት በአዋጁ አንቀጽ 56(2) እና አንቅጽ 57(7) መሰረት በይዘታቸው፣በባህሪያቸውና
በዓላማቸው የአባላቱን ጥቅም ከማስከበር ጋር የተያያዘ በመሆኑ በስብስብ መከፋፈል
ሳያስፈልግ ለሁሉም ማህበራት የሚከተሉት ወጪዎች ዓላማ ማስፈፀሚያ ተብለው
ይወሰዳሉ፡፡

1. የአባላቱን አቅም ለመገንባት ለሚሰጡ ሙያዊ ስልጠናዎች የሚወጣ ወጪ
(ለስልጠና ለሚያገለግሉ ማቴሪያሎች ዝግጅት፣ለሰልጣኞች የሚከፈል የው ሎ
አበል)፤

2. ለአባላቱ የሚደረጉ ድጋፎች (የገንዘብ፣ ህክምና፣ ትምህርት፣ ምግብና መጠለያ እንዲሆም ሌሎች ቁሳዊ ድጋፎች)፣

3. ማህበሩን በተመለከተ ለሚታተሙ የህትመት ውጤቶች የሚከፈል ክፍያ፤

4. በምርጫ ዙሪያ ምርጫን ለመታዘብ የሚወጣ ወጪ፡ – (ለኢትዮጵያዊያን ማህበራት
ብቻ)

5. ማኀበሩ ምርት ወይም አገልግሎት ሰጪ ከሆነ የጥሬ ዕቃዎች ግዥ ወጪ፣

6. ለተለያዩ አጋር ማኀበራት የሚከፈል የአባልነት መዋጮ፤ www.abyssinialaw.com

16

7.የማኀበሩን ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ የሚወጣ ወጪ እና የአዳራሽ ወጪ፤

አባሪ 3

ህዝባዊ መዋጮ ለሚሰበስቡ የበጎ
አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማህበራት የአላማ
ማስፈጸሚያ ወጪዎች

ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማኀ በር የተቋቋመበትን ዓ ላማ ከግብ ለማድረስ
ለሚያካሂደው ህዝባዊ መዋጮ የመሰብሰብ ስራ ከሚኖሩት ወጪዎች የሚከተሉት ብቻ
የዓላማ ማስፈጸሚያ ወጪ ተብለዉ ይያዛሉ ::
1. ገቢዉን ለማሰባሰብ የሚሆን ምርትን ለማምረት ወይም አገልግሎት ለመስጠት

የሚሆኑ ጥሬ ዕቃዎች ግዢ፡፡
2.
ህዝባዊ መዋጮዉን ለማሰባሰብ የሚደረጉ የማስታወቂያ ክፍያ ፡፡
3.
ህዝባዊ መዋጮዉን ለማሰባሰብ የሚያገለግል የአዳራሽ ወይም የቦታ ኪራይ
ክፍያ፡፡
4.
ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ለደንበኞች ለማቅረብ የሚከፈል የትራንስፖርት
ወጪ፡፡
አባሪ
4
ግዴታዎች
የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበራት ግዴታዎች
1. ማንኛውም በጎ አድራጐት ድርጅት ወይም ማኀበር በዚህ መመሪያ በአንቀጽ 5
ከተገለፁት ስብስቦች አንድና ከአንድ በላይ በሆነ ስብስቦች ላይ ተመስርቶ የሚሰራ
ከሆነ፤ ከተመሰረተበት ዓላማ አግባብነት ካላቸው በመለየት አግባብነት ያላቸዉን
ስብስቦች ስር የተገለጹትን ዓላማ ማስፈጸሚያ ወጪዎች ከግምት ው ስጥ በማስገባት

ከዚህ መመሪያ ጋር ተያይዞ ካለው አባሪ 1 ስር በተቀመጠው ዝርዝር መሠረት
በበጀት ዓመቱ ያቀደውን ስራና ለእቅዱ ማስፈጸሚያ የመደበው ን ወጪ ከጠቅላላው
ወጪው ከ70 በመቶ የማያንሰውን ለዓላማ ለማስፈፀሚያ እና ከ30 በመቶ
የማይበልጠውን ለአስተዳደራዊ ሥራ መመደቡን በመዘርዘር በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ
3ዐ ቀናት ውስጥ ለኤጀንሲው ማቅረብ ይጠበቅበታል፣
2. ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማኀበር ለኤጀንሲው ባቀረበው ዕቅድ ላይ
ዓላማ ማስፈፀሚያና አስተዳደራዊ ወጪውን በተመለከተ ማስተካከያ እንዲያደርግ
ኤጀንሲው በጽሑፍ ሲያዘዉ ትዕዛዙ በደረሰው 15 ቀናት ውስጥ ማስተካከያውን ማቅረብ
ይኖርበታል፡፡
3. ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማኀበር በአመቱ መጨረሻ ለኤጀንሲው
የሂሳብ መግለጫና የኦዲት ሪፖርት ሲያቀርብ ከጠቅላላ ዓመታዊ በጀቱ 70 ከመቶ www.abyssinialaw.com

17
የማያንሰውን ለአላማ ማስፈፀሚያ ማዋሉ እንዲሁም ከወጪው 30 ከመቶ
የማይበልጠውን አስተዳደራዊ ወጪ ማዋሉ የሚሰላዉ እያንዳንዱን ፕሮጄክት
አፈጻጸም በተናጥል ሳይሆን በሁሉም ኘሮጀክቶች ካዋለዉ የበጀት አፈጻጸም አንጻር
ነዉ።

4. ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማኀበር የተለያዩ እርከን ካላቸው
የመንግስት አካላት፤ወይም ከዘርፍ አስተዳዳሪ ዎች በመስማማት በአንድ አካባቢ ወይም
ክልል ተሰማርቶ የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል ለማገልገል ሲንቀሳቀስ ለስራው የመደበው
በጀት ለተጠቀሱት አካላት ግልጽ የማድረግ
ግዴታ አለበት፡፡
5. ማንኛውም የበጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማህበር የሂሳብ ሰራተኛ ወይም የውስጥ
ኦዲተር ወይም የውጭ ኦዲተር በአዋጁ አንቀጽ 79 እና 80 አንዲሁም በደንቡ አንቀጽ
21 አና 22 የተቀመጡ ድንጋጌዎችን አክብሮ አመታዊ የስራና የኦዲት አፈፃፀም
ሪፖርቱን ማዘጋጀት ይጠበቅበታል፤
6. ማንኛውም ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማኀበራት የገንዘብ ወይም የዓይነት
ድጋ

ፍ በማድረግ የሚሰራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ህብረት ወይም ማህበር ለበጎ
አድራጎት ድርጅ ቶች ወይም ማህበ ራት የገንዘብ ወይም የአይነት ድጋፍ ሲያደርግ
በቅድሚያ የገንዘብ ወይም የዓይነት ድጋፍ የሚደረግለት ድርጅት ያገኘው የድጋፍ
ገንዘብ ሊያውለው በፈለገው ኘሮግራም ወይም ኘሮጀክት ላይ ከ30% ያልበለጠው ን
ለአስተዳደራዊ ወጪ ከ70% ያላነሰዉን አላማ ማስፈፀሚያ ወጪ ለማዋል ስምምነት
ላይ መድረሱንና ማዋሉን የማረጋገጥ ግዴታ አለበት፡፡
7. ማንኛውም የገንዘብ ወይም የዓ ይነት ድጋፍ የሚያደርግ የውጭ ወይም የኢትዮጵያ
ነዋሪዎች የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር ለኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት
ወይም ማህበር ከ10 ከመቶ በላይ በገንዘብም ሆነ በዓይነት ድጋፍ ሊሰጥ አይችልም፡፡
8. ከላይ በንዑስ አንቀጽ 7 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ ለኢትዮጵያ በጎ አድራጎት
ድርጅት ወይም ማህበር 10 በመቶ የሚሆን በገንዘብ ወይም በአይነት ድጋፍ ማድረግ
የሚችለው ከሌላ ተመሳሳይ የውጭ ምንጭ ድጋፍ አለማግኘቱን በማረጋገጥ ይሆናል፡
9. ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር ኤጀንሲው ተጨማሪ መረጃ
እንዲቀርብባቸው የሚፈለጉ ጉዳዮች ወይም ተጨማሪ ማጣራት በማስፈለጉ ለሚደረግ
ምርመራ የበጐ አድራጐት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ወይም የስራ መሪ ወይም ሰራተኛ
መረጃ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
የኤጀንሲው ግዴታዎች www.abyssinialaw.com

18
1.
ማንኛውም የኤጀንሲው የምዝገባ ፤የክትትልና ድጋፍ ወይም ኦፊ ሰር በየዓመቱ
የሚቀርበውን የበጎ አድራጐት ድርጅት ወይም ማኅበር አመታዊ የበጀት
ዕቅድ፣የሂሰብ መግለጫ ወይም የሂሳብ ምርመራ ሪፖርት ሲገመግም ይህን
መመሪያ መሰረት የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
2. ማንኛውም የኤጀንሲው የምዝገባ፣ የክትትልና ድጋፍ ወይም ኦፈሰር የበጎ
አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት በበጀት አመቱ መጀመሪያ የሚያቀርቡትን
የስራ እቅዶቻቸውን ሲያቀርቡ ለአስተዳደራዊ ወጪ የተመደበዉ ከ30 በመቶ
ያልበለጥ ለአላማ ማስፈፀሚያ የተመደበዉ ከ70 በመቶ ያላነሰ መሆኑን
በመመርመር ማረጋገጥ ይገባዋል ፡፡
3. በተራ ቁጥር 2 በተገለጸዉ መሰረት በአቀረቡት ዓመታዊ ዕቅድ የአላማ
ማስፈፀሚያና የአስተዳደራዊ ወጪያቸውን በህጉ መሰረት አሟልተው ያላቀረቡ
ድርጅቶች አሟልተው እንዲያቀርቡ የማስተካከያ አስተያየት በጽሑፍ አዘጋጅቶ
በመስጠት ለበጐ አድራጐት ድርጅቶች ወይም ማኀበራቱ
ማሳወቅ አለበት፡፡
4. ኤጀንሲ ው ተጨማሪ መረጃ ማቅረብ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘዉ
የሚመለከተዉን
የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማኀበር እንደአስፈላጊነቱ የጽሑፍ ማብራሪያ
እንዲሰጠው ጊዜ ወስኖ ያሳውቃል፡፡
5. ኤጀንሲው ተጨማሪ ምርመራው እንዲካሄድ ሲወስን ምርመራው በኤጀንሲው
ሙያተኞች ወይም ኤጀንሲው ኦዲተር መድቦ እንዲመረመር ሊያደርግ ይችላል፡፡
6. የኤጀንሲው ሙያተኞች ወይም በኤጀንሲው የሚመደቡ ኦዲተሮች በማንኛውም
ጊዜ የድርጅቱን ወይም ማህበሩን የስራ አፈፃፀም፣ የሂሳብ መግለጫና የኦዲት
ሪፖርት ሲመረምሩና የማጣራት ስራ ሲያከናውኑ ሙያው በሚጠይቀው ስነ
ምግባር ስራቸውን ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡
7. በንዑስ አንቀጽ 6 የተቀመጠው እንደተጠበቀ ሆኖ ከሙያዊ ስነ ምግባር ውጭ
በሆነ መንገድ ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማኀበራት ሕገ ወጥ ጥቅም
በመፈለግ ወይም በመቀበል ኃላፊነቱን በማይወጣ የኤጀንሲው ሠራተኛ ላይ
ኤጀንሲው እንደ ጥፋቱ ደረጃ ቅጣት ይጥላል፡፡
የተለያዩ አካላት ግዴታዎች
መመሪያውን በመተግበር ሂደት፡ –

1. በአዋጁ አንቀጽ 67 ንዑስ አንቀጽ (2) እና (3) በተደነገገው መሠረት የዘርፍ
አስተዳዳሪዎች የበጎ አድራጐት ድርጅቶችና ማኅበራትን ፕሮግራሞችና www.abyssinialaw.com

19
ፕሮጀክቶችን ሲገመግሙ፣ ስምምነት ሲፈራረሙ እና አጠቃላይ የሥራ
እንቅስቃሴዎችን ሲቆጣጠሩ ለዓላማ ማስፈፀሚያ የተመደበው በጀትና አፈጻጸመሙ
70 ከመቶ ያላነሰ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡

2. በንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰውን መሰረት በማድረግ የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም
ማኀ
በሩ ለዓ ላማ ማስፈጸሚያ የተደረገዉን በጀት 70 ከመቶ መርህ ተከትሎ
መፈጸሙን ይከታተላሉ፤ አስፈላጊ ሲሆንም ለኤጀንሲው ማሳወቅ ይገባቸዋል፡፡
ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማኀ በር፤ የመንግስት አካላት፤ግለሰቦች
ይህንን
መመሪያ ከሚጥሱ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች መተባበር የለባቸውም፡፡
www.abyssinialaw.com