Directive to Provide for the Liquidation, Transfer and Dissolution of Properties of Charities and Societies No. 6

For optimal readability, we highly recommend downloading the document PDF, which you can do below.

Document Information:


የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት
ንብረቶችን
ለማጣራት፣ ለማስተላለፍ እና ለማስወገድ
የወጣ
መመሪያ
ቁጥር 6/2003

ነሐሴ 21 ቀን 2003 ዓ.ምwww.abyssinialaw.com


 

የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ንብረቶችን
ለማጣራት፣ ለማስተላለፍ እና ለማስወገድ የወጣ
መመሪያ
መግቢያ
የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራትን ለመመዝገብና ለማስተዳደር በወጣው አዋጅ 621/2001 እና በደንብ ቁጥር
168/2001 መሠረት ሕብረተሰብን ተጠቃሚ ለማድረግ የተቋቋመ የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር በሕግ አግባብ
ሲፈርስ ወይም በተለያየ ምክንያት ድርጅቱ የማይጠቀምበት ንብረት ሆኖ ሲገኝ በሕዝብ ስም ያሰባሰበው ሃብትና ንብረት
በድርጅቱ ጥያቄ ወይም በኤጀንሲው ውሳኔ ለተመሳሳይ ዓላማ ማዋል እንዲቻል ንብረቱን ለማጣራት፣ ለማስተላለፍ እና
ለማስወገድ የሚረዳ ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ
ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ፡፡
በህግ ያልፈረሱና በሥራ ላይ ያሉ በርካታ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ለረጅም ጊዜ የተገለገሉባቸውና በእርጅና
ምክንያት አገልግሎት የማይሰጡ ወይም ጊዜያቸው በማለፉ ምክንያት የማይፈለጉ ዕቃዎችን ለማስወገድ ለኤጀንሲው
የሚያቀርቡት የይወገድልን ጥያቄን ለማስተናገድ እንዲቻል ዝርዝር የማስፈፀሚያ ስርዓት ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ፡፡
በሌላ በኩል የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር በተጠቃሚው ህዝብ ስም ከቀረጥ ነፃ የገቡና የኮድ
35 አገልግሎት
ሽፋን የተሰጣቸው ተሸከርካሪዎችን ስርዓት ባለው መንገድ ለማስተዳደር፣ለማጣራት፣ለማስተላለፍ እና ለማስወገድ ይቻል
ዘንድ ግልፅ መመሪያ መኖሩ አስፈላጊ በመሆኑ፡፡
የኢፌድሪ በጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራትን ለመመዝገብና
ለማስተዳደር በወጣው አዋጅ ቁጥር 621/2001 አንቀጽ 9/4/ መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

www.abyssinialaw.com


 
ክፍል አንድ
ጠቅላላ
አንቀጽ 1. አውጭው ባለስልጣን
የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 621/2001 መሠረት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት
ንብረቶችን ለማጣራት፣ ለማስተላለፍ እና ለማስወገድ በአዋጁ አንቀጽ 9(4) በተሰጠው ስልጣን መሠረት ይህን መመሪያ
አውጥቷል፡፡
አንቀጽ 2. አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ “ የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ንብረቶችን ለማጣራት ለማስተላለፍ እና ለማስወገድ የወጣ መመሪያ
ቁጥር 6 /2003 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
አንቀጽ 3. ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ ያሉ ቃላትና ሐረጐች የሚከተለውን
ትርጉም ይይዛሉ፡ –
1. “አዋጅ ” ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራትን ለመመዝገብና ለማስተዳደር የወጣ አዋጅ ቁጥር
621/2001 ነው፡፡
2. “ደንብ ” ማለት ስለበጐ አድራጐት ድርጅቶች እና ማህበራት ምዝገባና አስተዳደር የወጣ የሚንስትሮች ም /ቤት
ደንብ ቁጥር 168/2001 ነው፡፡
3. “ኤጀንሲ ” ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ነው፡፡
4. “ቦርድ ” ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና

ማህበራት ቦርድ ማለት ነው፡፡
5. “ዋና ዳይሬክተር ” ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ነው፡፡
6 . “ ሿሚው አካል” ማለት ኤጀንሲው ወይም በኤጀንሲው ውክልና የተሰጠው በክልሎች የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና
ማህበራትን ለመምራትና ለማስተዳደር ህጋዊ ስልጣን የተሰጠው አካል ወይም በሕግ ሥልጣን ያለው
ፍርድ ቤት
ነው፡፡
7 . “ ንብረት አጣሪ ” ማለት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 6 በተዘረዘሩት አካላት ንብረትን ለማጣራት የሚሾም አካል
ነው፡፡
8 . “ ንብረት ማጣራት ” ማለት በሕግ አግባብ ንብረቱ እንዲጣራ ውሳኔ የተላለፈበትን የበጐ አድራጐት ድርጅት ወይም
ማህበር ሃብትና ዕዳ የመለየት ሂደት ነው፡፡
9 . “ ንብረት ማስተላለፍ ” ማለት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የተጣራውን ኃብትና ንብረት ለሌላ ወገን
የማስተላለፍ ሂደት ነው፡፡
10 . “ቋሚ ንብረት ” ማለት ግዙፋዊ ኃልዎት ያለው ከአንድ ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ የጠቀሜታ እሴት የሚኖረው እና
አገልግሎት በመስጠ

ት ላይ የሚገኝ ወይም ሊሰጥ የሚችል ንብረት ሲሆን እንደ የቢሮ ዕቃ፣ ኮምፒውተር፣
ተሽከርካሪ፣ መርከብ፣ አውሮፕላን፣ ህንፃ፣ እና የመሳሰሉትን ይጨምራል፡፡ www.abyssinialaw.com


 
11 . “ አላቂ ዕቃ” ማለት ከቋሚ ዕቃ ውጭ የሆነ ማናቸውም የበጐ አድራጐት ድርጅቶች ወይም ማህበራት ንብረት ሲሆን
ጥቅም ላይ መዋል ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አንድ ዓመት አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል እና ዋጋው የንብረት
አጣሪው በሚያወጣው የዋጋ ግምት የሚወሰን ንብረት ነው፡፡
12. “የዋጋ ግምት” ማለት በንብረት ማጣራት እና ማስወገድ ሂደት አጣሪው ወይም ልዩ ዕውቀት ያለው ባለሞ

ለአንድ ንብረት የሚሰጠው የዋጋ ተመን ነው፡፡
13. በዚህ መመሪያ በወንድ ፆታ የተደነገገው የሴትንም ፆታ ያካትታል፡፡
አንቀጽ 4. የመመሪያው ተፈፃሚነት ወሰን
ይህ መመሪያ በሚከተሉት ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
1. በህግ አግባብ መሠረት በሚፈርሱ የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ሀብትና ንብረት፤
2. በተቋረጡ ወይም በተጠናቀቁ የበጐ አድራጐት ድርጅቶች ወይም ማህበራት ፕሮጀክቶች ሀብትና ንብረት፤
3. በቂ ባልሆነ ወይም ከሚፈለገው በላይ የተሰበሰበ የበጐ አድራጐት ኮሚቴ ሀብትና ንብረት፤
4. በኤጀንሲው በተሰረዙ የገቢ ማስገኛ እና ሕዝባዊ መዋጮ ፈቃዶች በተገኘ ሀብትና ንብረት፤
5. በአዋጁ አንቀጽ 95 መሠረት የበጐ አድራጐት ድርጅቶች ንብረትን ለተቀራራቢ ዓላማ ለማዋል በሚሰጥ
ውሳኔ፤
6. የአገልግሎት ዘመናቸ

ውን በጨረሱ፣ ከሚሰጡት አገልግሎት ጉዳታቸው ያመዘነ የበጐ አድራጐት ድርጅት
ወይም ማህበር ንብረት፤
7. በአዋጁ አንቀጽ 97 /1/ ሀ መሠረት የአነስተኛ የበጐ አድራጐት ድርጅቶች ሀብትና ንብረት ለሌላ እንዲተላለፍ
ወይም እንዲከፋፈል በሚሰጥ ውሳኔ፡፡
8. በደንቡ አንቀፅ 18 መሰረት ከውጭ በጎ አድራጐት ድርጅት ወይም ከኢ
ትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጐት
ድርጅት ወይም ማህበር ወደ ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር በሚቀየሩ የበጎ አድራጎት
ድርጅቶችና ማህበራት ሃብትና ንብረት፡፡
አንቀጽ5. የመመሪያው ዓላማ
በህግ አግባብ እንዲጣራ የተወሰነውን የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ገንዘብና ንብረት ውጤታማ፣ ዘመናዊና
ቀልጣፋ በሆነ መልኩ ለሌላ ተጨማሪ ሕዝባዊ አገልግሎት እንዲውል፤ እንዲሁም በልዩ ልዩ ምክንያት ከአገልግሎት ውጭ
የሆነውን ወይም አገልግሎት መስጠት የማይችለውን የበጐ አድራጐት ድርጅቶችን ወይም ማህበራትን ንብረት በወቅቱና
በተገቢው መንገድ እንዲወገድ ማስቻል ነው፡፡
www.abyssinialaw.com


 
ክፍል ሁለት
የአጣሪዎች አሿሿም
አንቀጽ 6. ንብረት አጣሪዎችን የመሾም ስልጣን
1. በህግ አግባብ የበጐ አድራጐት ድርጅቶች ወይም ማህበራት ሀብትና ንብረትን ለማጣራት ኤጀንሲው ወይም ፍርድ
ቤት ንብረት አጣሪ የመሾም ስልጣን ይኖራቸዋል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የየክልሉ የበጎ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራትን
ለመመዝገብና ለማስተዳደር ህጋዊ ስልጣን ያለው አካል ኤጀንሲው በሚሰጣቸው ውክልና መሰረት ንብረት አጣሪን
የመሾም ይኖረዋል፡፡
3. አጣሪዎች የሚሾሙት በሙሉ ፈቃደኝነትና ፍላጐት ይሆናል፡፡ያለው አካል ኤጀንሲው በሚሰጣቸው ወክልና

መሰረት ንብረት አጣሪን የመሾም ስልጣን
አንቀጽ 7. የአጣሪዎች ስብጥር
1. የአጣሪ ኮሚቴ አባላት ከኤጀንሲው ሰራተኞች፣ ወይም ንብረቱ ከሚጣራበት ድርጅት ወይም ማህበር የስራ
መሪዎችና ሰራተኞች፣ ወይም ለማጣራት ስራ አስፈላጊ ከሆነ አግባብነት ካላቸው የዘርፍና የክልል መንግስታዊ
ተቋማት ወይም መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ሊውጣጡ ይችላሉ፡፡
2. የአጣሪ ኮሚቴ አባላት እንደሚጣራው ንብረት ስፋትና ብዛት በሿሚው አካል የሚወሰን ሆኖ ቁጥራቸው ከ 3-5
ሊደርስ ይችላል፡፡
አንቀጽ8. አጣሪዎችን ለመሾም የሚያስፈልገው መስፈርት
1. መልካም ሥነ – ምግባር ያለው፣ ሥራውን በሚገባ ለመፈጸም የሚያስችል አስፈላጊ የሞያ ብቃትና ክህሎት ያለው፤
2. ከማጣራት ሥራው ጋር በተገናኘ ምንም አይነት የጥቅም ግጭት የሌለው፤
3. በማጭበርበር፣ ስርቆት፣ ዕምነት ማጉደል እንዲሁም ከንብረት ጋር በተያያዘ በሌሎች ወንጀሎች ተከሶ ያልተቀጣ፤
4. የአጣሪዎች የሞያ ስብጥር ቢያንስ በንብረት አስተዳደር ወይም በሂሳብ አያያዝ ወይም በሥራ አመራር ወይም በህግ
ሙያ የተመረቁ ባለሞያዎችን የሚያካትት

ይሆናል፤
5. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 4 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ኤጀንሲው ለማጣራት
ስራ ተገቢ ነው ብሎ ያመነውን ሌላ ሙያተኛ ሊመድብ ይችላል፡፡
አንቀጽ 9. አጣሪዎች የሚሾሙበት ጊዜ
1. አጣሪዎች የአንድ በጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማህበር የንብረት ማጣራት ውሳኔ በተሰጠ በ 15 ቀናት ጊዜ
ውስጥ ይሾማሉ፡፡
2. አጣሪው መሾሙን የሚገልጽ ደብዳቤ በሿሚው አካል ተፈርሞ ሲደርሰው ሥራውን ይጀምራል፡፡
3. የማጣራት ሥራው እሰከ 2 ወር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ሆኖ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በሿሚው አካል ውሳኔ ሊራዘም
ወይም ሊያጥር ይችላል፡፡ www.abyssinialaw.com


 
አንቀጽ 10 የአጣሪዎች አመራር ስልጣንና ተግባር
1. ያጣሪ ቁጥር ከ2 በላይ ሲሆን የአጣሪው ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢና ፀሃፊ የሚሆኑት በሿሚው አካል ይሾማሉ፡፡
2. የአጣሪው ኮሚቴ ሰብሳቢ
ሀ . የአጣሪነቱን ሥራ በበላይነት ይመራል፣ ይቆጣጠራል፤
ለ . መደበኛና አስቸኳይ ስብሰባ ይጠራል፤
ሐ . የኮሚቴውን ስብሰባ ይመራል፤
መ . ኮሚቴው የወሰናቸውን ውሳኔዎች በትክክል ሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፤
ሠ . የአጣሪ ሥራዎችን ወቅቱን ጠብቆ ለሾመው አካል ሪፖርት ያቀርባል፡፡
3. ምክትል ሰብሳቢ
ሀ. ሰብሳቢው በማይኖርበት ጊዜ ተክቶ ይሰራል፤
ለ . በሰብሳቢው የሚሰጡ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
4. ፀሐፊ
ሀ. ከሰብሳቢው ጋር በመሆን የስብሰባውን የመወያያ አጀንዳዎችን ይቀርፃል፤ ቃለ – ጉባኤዎችን ይይዛል፤
ለ .. ከማጣራት ሥራዎች ጋር የተያያዙ ሰነዶችን በአግባቡ ይይዛል፡፡
አንቀጽ11. የስብሰባ ሥነ- ሥርዓት
1. አጣሪዎች በሚያደርጉት ሥምምነት ወይም በሚያወጡት ዕቅድ መሠረት መደበኛና አስቸኳይ ስብሰባ
ይኖራቸዋል፡፡
2. የኮሚቴው 50+1 አባላት ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤው እንደተሟላ ይቆጠራል፡፡
3. ውሳኔዎች በድምፅ ብልጫ ይተላለፋሉ፤ ድምፅ እኩል ከሆነ የሰብሳቢው ድምፅ ገዥ ይሆናል፡፡
4. አጣሪዎች የልዩነት ኃሳባቸውን በቃለ ጉባኤ ማስፈር ይችላሉ፡፡
5. የስብሰባ ቃለ – ጉባኤዎች ቅጅ በሁሉም አባላት ተፈርሞና ከፈረሰው ድርጅት ሰነድ ጋር ተያይዞ በኤጀንሲው ጽ /ቤት
ይቀመጣል፡፡
አንቀጽ12. የአጣሪዎች ሥነ – ምግባር
1. ከማጣራት ሥራው ጋር በተገናኘ ምንም አይነት የወንጀል ድርጊት አለመፈጸም፤
2. በሚጣራው ኃብትና ንብረት ላይ ምንም አይነት ብክነት እና ምዝበራ አለማድረስ፤
3. ከማጣራት ሥራው ጋር ምንም አይነት ሥጦታ ወይም የገንዘብ ዋጋ ያለው ነገር ወይም አገልግሎት አለመቀበል፤
4. ከማጣራት ሥራው ጋር በተገናኘ የግድ በምስጢር መጠበቅ ያለባቸውን መረጃዎች ጠብቆ ማቆየት፤
5. በማጣራቱ ሥራ ሂደት ሊፈጠሩ የታሰቡ ወይም የተፈጠሩ የሙስና ተግባራ
ትና ብልሹ አሠራሮችን አጥብቆ
መታገልና ለሚመለከታቸው የፍትህ አካላት በየደረጃው ማሳወቅ፤
6. ከማጣራት ሥራው ጋር በተያያዘ የተፈጠረ ወይም ሊፈጠር የሚችል የጥቅም ግጭትን ለሾመው አካል በጽሁፍ
በማሳወቅ ራሱን ከማጣራት ሂደቱ ማግለል፤
7. የድርጅቱን ወይም የማህበሩን ንብረቶች እንዳይመዘበሩ፣ እንዳይባክኑና እንዳይበላሹ ልክ እንደ መልካም አባት
ሆኖ እንዲጠበቅና እንዲቀመጥ ማድረግ፣
8. አጣሪዎች የሚጣራውን ሃብት እንደ መልካም አባት ሆነው ይሰራሉ www.abyssinialaw.com


 

አንቀጽ 13. የአጣሪዎች ስልጣንና ተግባር
1. ንብረትን የማጣራትና የማስተላለፍ ሥራቸውን ነፃና ገለልተኛ ሆነው መሥራት፤
2. የማጣራት ሥራቸውን ለማከናወን እንዲረዳቸው አግባብነት ያላቸውን ማናቸውንም ሰነዶችና ማህደሮች አስቀርቦ
የመመርመር መረጃ የመሰብሰብና የማጠናከር እንዲሁም የሚመለከታቸውን የሥራ መሪዎች ቀርበው እንዲያስረዱ
ማድረግ፤
3. በንብረት ማጣራትና በማስተላለፍና ሂደቱ ተገቢ ሆኖ ሲያገኙት መንግስታዊ ወይም መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ልዩ
ሙያዊ እገዛ መጠየቅና ማግኘት፤
4. ከድርጅቱ ወይም ማህበሩ ለማጣራት ሥራው መነሻ ሊሆን የሚችል የኦዲት/የሂሳብ / ሪፖርት፣ የንብረት ዝርዝር፣
የባንክ ሂሳብ መግለጫ

እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ሰነዶች እንዲቀርብላቸው ማዘዝ፤
5. የማጣራት ስራ የሚከናወንበት የበጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማህበር ይዞታ ስር የሚገኝ ማንኛውንም ንብረት
ማሸግ፣
6. ለማጣራት የሚያግዙ ማንኛውንም የድርጅቱን ወይም የማህበሩን ሰነድ በኃላፊነት ተቀብሎ መያዝ፤
7. የድርጅቱን ወይም የማህበሩን ቋሚና አላቂ ንብረት ዝርዝር
(assets inventory) ማዘጋጀት፤
8. ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ያሉትን ኃብቶችና ያሉበትን ዕዳዎች ለይቶ በማወቅ ዝርዝር የሃብትና የዕዳ ሚዛን (Balance
Sheet) ማዘጋጀት፤
9. የድርጅቱን ወይም ማህበሩን ገቢና ወጭ ለይቶ በማስላት የሂሳብ መግለጫ (financial statement) ማዘጋጀት፤
10. የድርጅቱ የሃብት መጠን የግድ በውጭ ኦዲተር መመርመር ያለበት መሆኑን
የሚያሳይ ከሆነ በድርጅቱ ወይም ማህበሩ የገንዘብ ወጪ ሃብትና ዕዳው፣ ገቢና
ወጪዎች በውጭ ኦዲተር እንዲመረመር ያ

ስደርጋል፤
11. ይበላሻሉ ወይም ለከፍተኛ ወጪ ይዳርጋሉ ተብለው የታሰቡ ንብረቶችን ህጋዊ
በሆኑ አሰራሮች በገበያ ዋጋ ተሽጦ በበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ስም በባንክ በዝግ ሂሳብ
እንዲቀመጥ ማድረግ፤
12. የሚጣሩ በበጎ አድራጎት ድርጅቱን ወይም የማህበሩን ንብረቶች እንዳይመዘበሩ
13. እንዳይባክኑና እንዳይበላሹ ልክ እንደ መልካም አባት እና እንደራሱ አድርጎ
እንዲጠበቅና እንዲቀመጥ ማድረግ


14. አጣሪው የበጎ አድራጎት ድርጅቱን የድርጅቱን ወይም የማህበሩን ሀብት
ከምዝበራ፣ ከብክነትና ከብልሽት ለመጠበቅ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በአንድ ቦታ
መሰብሰብና ከሀብቱ የሚመነጩ ልዩ ልዩ ገቢዎችን መቀበል፣
15. የድርጅቱን ወይም ማህበሩን ልዩ ልዩ ወጪዎች፣ ዕዳዎች ማስረጃን መሠረት
በማድረግ መክፈል ወይም እንዲከፈል ማድረግ፣ ደረሰኝ መስጠትና መቀበል፤
16. ከማጣራት ሥራው ጋር በተገናኘ እንደየ አስፈላጊነቱ ውል መግባት፣ ፍ /ቤት ቀርቦ
መከራከርና ውክልና መስጠት፤
17. የማጣራት ሥራው ከተጠናቀቀና ወጪዎችና ዕዳዎች

ም ተከፍለው ካበቁ በኋላ
ቀሪውን ሀብት በዚህ መመሪያ መሠረት ለሚገባው አካል ማስተላለፍ፤
18. ንብረት የማጣራትና የማስተላለፍ ሥራውን በተመለከተ በየጊዜው ወቅቱን ጠብቆ www.abyssinialaw.com


 
ለሾመው አካል ሪፖርት ማድረግ፤
19. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 18 ላይ የተመለከቱትን ሥራዎች በተገቢው መልኩ
ለማሳካት አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ተግባሮችን መፈፀም፡፡
አንቀጽ14. የአጣሪዎች ክፍያ
1. አጣሪዎች ከማጣራት ስራ ጋር በተያያዘ ለሚሰጡት አገለግሎት ክፍያ አይታሰብላቸውም፡፡
2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው ቢኖርም ከኤጀንሲው ሰራተኛ በስተቀር ንብረት አጣሪ ሆነው
ለሚመደቡ ሠራተኞች የማጣራት ሥራውን ለማከናወን ምክንያታዊ ለሆኑ ወጪዎች ከሚጣራው ንብረት ላይ
የሚተካ በአበል መልክ እንዲከፈላቸው ሊደረግ ይችላል፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 የተመለከቱትን ወጪዎች የሚጣራው ንብረት ወጪዎቹን ሊሸፍን የማይችል ከሆነ
ሿሚው አካል ይሸፍናል፡፡
አንቀጽ15. አጣሪዎችን ማንሳትና መተካት
አንድ አጣሪ በማንኛውም ምክንያት የአጣሪነት ሥራውን መሥራት አለመቻሉን ሿሚው አካል ሲያረጋግጥ ሹመቱን
በደብዳቤ ይሽራል፤ ተተኪውንም በተመሳሳይ መንገድ ይሾማል፡፡
አንቀጽ16. የንብረት አጣሪዎች የሕግ ተጠያቂነት
1. አንድ አጣሪ ከማጣራት ሥራው ጋር በተያያዘ ይህንን መመሪያ በመተላለፍ የወንጀል ድርጊት ፈጽሞ ከተገኘ
በወንጀል ህግ ድንጋጌዎች መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡
2. ማንኛውም አጣሪ አስቦ ወይም በቸልተኛነት ወይም ባለመጠንቀቅ በሚጣራው ንብረት ላይ ለሚደርሰው ጉዳት
በፍትሐብሔር ተጠያቂ ይሆናል፡፡ www.abyssinialaw.com


 
ክፍል ሶስት
የንብረት ማጣራት ሥርዓት
አንቀጽ17. የቅድመ ማጣራት ሥራ
1. አጣሪዎቹ ለማጣራት ሥራው የሚያግዙ የኦዲት ሪፖርቶች፣ የንብረት ዝርዝር፣ የባንክ ሂሳብ መግለጫና ሌሎች
አስፈላጊ የንብረትና የሂሳብ ሰነዶችን ከኤጀንሲው፣ ከበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ዋና መ /ቤት፣
በቅርንጫፍ ጽ /ቤቶች፣ የፕሮጀክት ቦታዎች ከተጠቃሚዎችና ከማንኛውም ተቆርቋሪ ዜጋ እንዲሁም ሌሎች
መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች በማሰባሰብ ይመረምራሉ፡፡
2. የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም የማህበሩ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በእጃቸው የሚገኝ
የሂሳብ ወይም
የንብረት ሰነድ ካለ እንዲያስረክቡ እንዲሁም ስለሚጣራው ሀብት ተገቢውን መረጃ እንዲሰጡ አጣሪዎች ሊያዙ
ይችላሉ፡፡
3. አጣሪዎች ከማጣራት ሂደቱ በፊት የተሰበሰቡትን ሰነዶች ህጋዊነትና ዕውነተኛነት ከሚመለከታቸው
መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ያረጋግጣሉ፡፡
4. አጣሪዎች የሚጣራውን ንብረት ከሚመለከታቸው የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም የማህበሩ አመራሮች ወይም
ህጋዊ ወኪሎቻቸው የተረከቡ ስለመሆናቸው በህጋዊ የመረከቢያ ደረሰኝ ቆርጠው በመስጠት ያረጋግጣሉ፡፡
5. ንብረት አስረካቢው ድርጅት ወይም ማህበር ንብረቱን ያስረከበበትን ፅሁፍ ደረሰኝ ይዞ ሲቀርብ

ከኤጀንሲው
የማረጋገጫ ደብዳቤ ይሰጠዋል፡፡
አንቀጽ 18. ዝርዝር የማጣራት ሥራ
ዝርዝር የማጣራት ሥራው የሚከተሉትን ተግባራት ያካትታል፡ –
ሀ . ንብረቶችን ማሸግ፤
ለ . የንብረት ዝርዝር ማዘጋጀት፤
ሐ . የንብረት ግምት ማውጣት፤
መ . ንብረትን ወደ አንድ ቦታ ማሠባሠብ፤
ሠ . የድርጅቱን ወይም የማህበሩን ወጭዎችና ዕዳዎች መለየትና ቅደም ተከተል ማስያዝ፤
ረ . የሃብትና የዕዳ ሚዛን ማዘጋጀት፤
ሰ. የወጭና የገቢ መግለጫ ማዘጋጀት፤
አንቀጽ19. ንብረት ማሸግ
1. አጣሪዎች ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 ቀናት የድርጅቱን ወይም የማህበሩን ንብረት ባለበት ቦታና
ሁኔታ ታዛቢዎች በተገኙበት ያሽጋሉ፤
2. የእሽግ ሥራው በአጣሪዎች የቃለ – ጉባኤ ፊርማ ሥነ – ሥርዓት መከናወን ይኖርበታል፤
3. በመታሸጊያ ወረቀቱ ላይ የአጣሪዎች ፊርማና የኤጀንሲው ክብ ማህተም ይኖርበታል፡፡ www.abyssinialaw.com


 
አንቀጽ 20. የንብረት ዝርዝር ማዘጋጀት
1. አጣሪዎች ንብረቱ ከታሸገበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 10 ቀናት ንብረቶቹን በአይነታቸው በመለየት የንብረት ዝርዝር
መዝገብ ያዘጋጃሉ፡፡
2. በንብረት ምዝገባው ወቅት ሣይገኙ የቀሩ ንብረቶች የማጣራት ሥራው ሳይጠናቀቅ ከሆነ በተገኙበት ጊዜ ንብረት
ዝርዝሩ ውስጥ ተካተው ይመዘገባሉ፡፡
3. የማጣራት ሥራው ከተጠናቀቀ በኋላ ለሚገኝ ንብረት ለኤጀንሲው ሪፖርት ቀርቦ ኤጀንሲው የመጨረሻ ውሣኔ
ይሰጥበታል፡፡
አንቀጽ 21. ንብረትን ወደ አንድ ቦታ ማሰባሰብ
1. አጣሪዎች ሊሰበሰቡ የሚችሉ የድርጅቱን ወይም የማህበሩን ሀብትና ንብረቶች ለቁጥጥርና ለጥበቃ ያመቻል
ብለው ወደ ወሰኑት ቦታ ይሰበስባሉ፡፡
2. አጣሪዎች በንብረቱ ተፈጥሮአዊ ባህርይ ወደ አንድ ቦታ ሊሰበሰብ የማይችለውን ንብረት ባለበት ቦታ
እንዲጠበቅ ያደርጋሉ፡፡
3. ንብረቱ ከቆይታ አንፃር በቶሎ የሚበላሽ ከሆነ ወይም ከፍተኛ ወጪ የሚያስከትል ከሆነ በወቅቱ ኮሚቴው
ባጠናው የገበያ ዋጋ ተሽጦ በድርጅቱ ወይም በማህበሩ ሥም ገንዘቡ በዝግ ሂሳ
ብ እንዲቀመጥ ይደረጋል፡፡
አንቀጽ 22. የንብረት ዋጋ ግምት ማውጣት
1. አጣሪዎች የንብረቶቹን የዋጋ ግምት ንብረቱ ተሰባስቦ ከተጠናቀቀ በኋላ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ የዋጋ ግምት
ያወጣሉ፡፡
2. አጣሪዎች ዋጋ ሊያወጡላቸው ያልቻሉ ንብረቶችን ልዩ አዋቂዎችን ቀጥረው እንዲገመቱ ያደርጋሉ፡፡
አንቀጽ 23.
የ በጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም የማህበሩን ወጭዎችና ዕዳዎች መለየት
1. የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም የማህበሩ ወጭ ዕዳዎች እና የአከፋፈል ቅደም ተከተል፡ –
ሀ . የመጋዘን ኪራይ፣ የጥበቃ፣ የመጓጓዣ፣ የማስታወቂያ፣ የልዩ አዋቂ ንብረት ገማች፣ የጽህፈት አገልግሎትና
መሣሪያ፣
የኦዲት ምርመራ፣ የዳኝነት አገልግሎቶች እንዲሁም ከማጣራት ሥራ ጋር የተያያዙ ልዩ ልዩ ወጪዎች፤በአንደኛ
ደረጃ
ለ . የመንግስት ቀረጥና ግብር፣ ሥልክ፣ መብራት፣ ውሃና ሌሎች ልዩ ልዩ መንግስታዊ አገልግሎቶች የሚከፈሉ
ወጭዎችና ዕዳዎች፤በሁለተኛ ደረጃ
ሐ . ከድርጅቱ ወይም ማህበሩ የገንዘብ ጥያቄ ላላቸው ባለመብቶች የሚከፈሉ ዕዳዎችን ያጠቃልላል፡፡
2. የገንዘብ ጠያቂዎች (Creditors) ዕዳ አከፋፈል ቅደም ተከተል እንደሚከተለው ይሆናል፡ –
ሀ .

የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ተቀጣሪ ሠራተኞች ደመወዝና ልዩ ልዩ ክፍያዎች፤
ለ. ንብረት ያሳገዱ ወይም የንብረት መያዣ ያላቸው ባለመብቶች፤ www.abyssinialaw.com

10 
 
ሐ. የንብረት መያዣ ባይኖረውም ማንኛውም መብት አለኝ የሚል ወገን፤
3. እኩል ደረጃ ያሉ ባለመብቶች /ገንዘብ ጠያቂዎች / እንደ ሀብታቸው መጠን በመቶኛ ተስልቶ ዕዳቸው የሚከፈል
ይሆናል፡፡

አንቀጽ 24. የሀብትና የዕዳ ሚዛን ማዘጋጀት
አጣሪዎች የምርመራ ውጤታቸውን መሠረት አድርገው በጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ያለውን አጠቃላይ ሃብት፣
ያለበትን ዕዳ፣ ቋሚና አላቂ ንብረቶችን፣ ያልተሰበሰበና የሚከፈል ገንዘብ እንዲሁም ቀሪ ንብረትና ገንዘብ ለይቶ በማወቅና
በማስላት የሀብትና የዕዳ ሚዛን ያዘጋጃሉ፡፡
አንቀጽ 25. የገቢና ወጭ መግለጫ ማዘጋጀት
1. አጣሪዎች የሚጣራው ንብረት ከብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ / ብር በታች ሆኖ ሲገኝ ሿሚው አካል
በሚመድበው የውስጥ ኦዲተር እንዲመረመር ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
2. አጣሪዎች የሚጣራው ሀብት ከብር 100,000 / አንድ መቶ ሺህ/ በላይ ሆኖ ሲያገኘው ህጋዊ ዕውቅና ባላቸው
የውጭ ኦዲተሮች እንዲመረመር ያደርጋሉ፡፡
3. አጣሪዎች የራሳቸውን ወይም የኦዲተሩን ምርመራ መሠረት አድርገው በጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ
ከአገር ውስጥና ከውጭ ምን ያህል ገቢ እንዳገኘ፣ ለአስተዳደርና ለዓላማ ማስ

ፈጸሚያ ምን ያህል ወጪ እንዳወጣና
ከወጪ ቀሪ ምን ያህል እንደሆነ ለይቶ በማወቅና በማስላት የገቢና ወጪ መግለጫ ያዘጋጃሉ፡፡

አንቀጽ 26. በበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ባለመብቶች ወይም ገንዘብ ጠያቂዎች (Creditors)
ስለሚደረግ ማስታወቂያ

1. አጣሪዎች በመንግስታዊ ጋዜጣ ሥለ በጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ መፍረስ ይፋ ያደርጋሉ፤
2. ገንዘብ ጠያቂዎች በጎ አድራጎት የድርጅቱ ወይም ማህበሩ መፍረስ በጋዜጣ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15
ተከታታይ ቀናት የይገባኛል አቤቱታቸውን በጽሁፍ ለአጣሪዎች ያቀርባሉ፤
3. አጣሪዎች የቀረበላቸውን አቤቱታ መርምረው በ 5 ቀናት ውስጥ ውሣኔያቸውን በጽሁፍ ለአቤቱታ አቅራቢው
ይሰጣሉ፤
4. በውሳኔው ቅር የተሰኘ ባለመብት ውሣኔው በተሰጠ በ 10 ቀናት ውስጥ ለሿሚው አካል ይግ
ባኝ በጽሁፍ ያቀርባል፤
5. ሿሚው አካል የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የህግ ጥያቄ የሚያሰነሳ ሆኖ ሲገኝ
የፍርድ ቤት የይገባኝ መብቱ አያስቀረውም ።

አንቀጽ 27. የዕዳ አከፋፈል ስርዓት

1. የበጎ አድራጎትድርጅቱን ወይም ማህበሩን ወጪና ዕዳ ለመክፈል ቅድም ተከተሉ እንደሚከተለው ይሆናል፡-
ሀ . ጥሬ ገንዘብ፤
ለ . ጥሬ ገንዘቡ ካልበቃ ተራ ተንቀሳቃሽ ንብረት በመሸጥ፤
ሐ እንደ ተሽከርካሪ የመሳሰሉ ልዩ ተንቀሳቃሽ እና የማይንቀሳቀስ ንብረት አግባብነት ባለው ህግ መሰረት ተሽጦ
ይከፈላል፡፡
www.abyssinialaw.com

11 
 

ክፍል አራት
የንብረት ማስተላለፍ ሥርዓት

አንቀጽ 28. የተጣራው ሀብትና ንብረት ሪፖርት ስለማድረግ
አጣሪዎች የማጣራት ሥራው ተጠናቆ፣ ወጪዎችና ዕዳዎችም ተከፍለው ካበቁ በኋላ ቀሪውን ዝርዝር ንብረት በጽሁፍ
ለሿሚው አካል በ5 ቀናት ውስጥ ያቀርባሉ፡፡
አንቀጽ 29. ንብረት ወይም ሀብት ሥለማስተላለፍ
1. ወጭዎችና እዳዎች ተከፍለው ከተጠናቀቁ በኋላ የተገኘው ቀሪ ሀብትና ንብረት በሚከተለው ቅደም ተከተል
መሠረት፡-
ሀ . ተመሳሳይ ዓላማ ላለው በጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማህበር፤
ለ . ተቀራራቢ ዓላማ ላለው በጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማህበር፤
ሐ . ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ብሎ ኤጀንሲው ላመነባቸው ማህበራትና በጐ አድራጐት ድርጅቶች፤
መ . ከበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ጋር ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ዓላማ ላላቸውና ማህበራዊ አገልግሎት

ለሚሰጡ መንግስታዊ ተቋማት ይተላለፋል፤
2. የሚተላለፈው የንብረት መጠን ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ አጣሪዎች ሁለትና ከዚያ በላይ ለሆኑ በጐ አድራጐት
ድርጅቶችና ማህበራት ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡
3. አጣሪዎች የተጣራውን ሀብትና ንብረት ፈላጊ መስፈርቱ የሚያሟላ ካለ ንብረቱ በሚገኝበትና ሊነበብ በሚችል ቦታ
የጽሁፍ ማስታወቂያ ይለጥፋሉ፤ እንደነገሩ ሁኔታ በጋዜጣ ማስታወቂያ ማውጣትም ይችላሉ፡፡
4. ንብረት ፈላጊ ከበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ማስታወቂያ በወጣበት በ5 የሥ

ራ ቀናት ውስጥ ለንብረት
አጣሪው በጽሁፍ ያመለክታል፡፡
5. አጣሪዎች የንብረት ፍለጋ ጥያቄውን አሰባስበውና መርምረው በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ ውሳኔውን ንብረት
ፈላጊዎች ባመለከቱበት ቦታና በሿሚው አካል መ/ቤት ውስጥ የአሸናፊውን በጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር
ሥም ገልፀው ይለጥፋሉ፡፡
6. በአጣሪው ውሳኔ ቅር የተሰኙ ንብረት ፈላጊዎች ውሳኔው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ቅር
የተሰኙበትን ዝርዝር ምክንያት ለሿሚው አካል ያቀርባሉ፤ ለሿሚው አካል ከቀረበ በ15 ቀን ውስጥ ውሳኔ ይሰጣ


ወሳኔው የመጨረሻ ይሆናል፡፡

አንቀጽ 30. ንብረት የሚተላለፍለት በጎ አድድርጅት ድርጅት ወይም ማህበር ሊያሟላው የሚገባ
መስፈርት

1. ህጋዊ መስፈርቶች
ሀ . የአባላቱንና የሥራ መሪዎች ዝርዝርና ቋሚ አድራሻውን በየወቅቱ የሚያሳውቅ፤
ለ . የተሟላ ዓመታዊ የሥራና የኦዲት/የሂሳብ / ሪፖርት ጊዜውን ጠብቆ የሚያቀርብ፤
ሐ . የባንክ ሂሳቡን በህጉ መሠረት ለኤጀንሲው አሳውቆ የሚንቀሳቀስ፤
መ . ወቅታዊ ለውጦችን በየጊዜው ለኤጀንሲው የሚያሳውቅ፤ www.abyssinialaw.com

12 
 
ሠ . አዋጁን፣ ደንቡን እንዲሁም በኤጀንሲው የሚወጡ ልዩ ልዩ መመሪያዎችን በመተላለፍ የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያም ሆነ የዕገዳ ውሳኔ ያልተሰጠው፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አጣሪዎች የንብረት ፈላጊውን የዓላማ ተዛምዶ፣
ተቀራራቢነት፣ የሀብት አቅም እንዲሁም የጥያቄውን አቀራረብ የጊዜ ቅደም ተከተል አገናዝበው ሊወስኑ ይችላሉ፡፡
አንቀጽ 31. የሚተላለፍ ንብረት የርክክብ ሥርዓት
1. አጣሪዎች የንብረት ርክክብ በፅሑፍ በማዘጋጀት እማኞች ባሉበት ንብረቱ ለሚተላለፍለት ድርጅት ወይም ማህበር
በፊርማ ያስረክባሉ፡፡
ሀ . የርክክቡ በፅሑፍ 1 ቅጅ በተረካቢ፤
ለ . 1 ቅጅ በሿሚው አካል፤
ሐ . 1 ቅጅ በአጣሪዎች እጅ እንዲቀመጥ ይደረጋል፡፡
2. አጣሪዎች የንብረት ርክክብ ሥርዓት ዝርዝር ለሾመው አካል ሪፖርት ያቀርባሉ፡፡

አንቀጽ 32. በተላለፈው ንብረት ላይ የሚነሳ የባለቤትነት ጥያቄ
ንብረቱ የተላለፈላቸው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማህበራት ለሚያነሱት የባለቤትነት ማረጋገጫና ሌሎች ተዛማጅ
ጥያቄዎች ኤጀንሲው ለሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ አካላት ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
አንቀጽ 33. በተላለፈው ንብረት ላይ የሚነሱ የዕዳ ጥያቄዎች
1. በንብረት ማጣራት ሂደቱ ወቅት ያልቀረቡ ገንዘብ ጠያቂዎች ንብረቱ ከተላለፈለት በጎ አድራጎት ድርጅት ወይም
ማህበር በሕግ አግባብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ “1″ የተደነገገው ቢኖርም ንብረቱ የተላለፈለት በጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር
ከተረከበው የንብረት መጠን በላይ በዕዳ ሊጠየቅ አይችልም፡፡ www.abyssinialaw.com

13 
 
ክፍል አምስት
ንብረት የማስወገድ ስርዓት
አንቀጽ 34. ንብረት ማስወገድ
1. የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ንብረት በሚከተሉት ምክንያቶች ማስወገድ ይቻላል፡፡
ሀ . በእርጅና ምክንያት፤
ለ . በአደጋ ወይም በብልሽት ምክንያት፤
ሐ . ከሚሰጠው አገልግሎት የሚያስከትለው ወጪ ከፍተኛ ሆኖ ሲገኝ፤
መ . በሰውም ሆነ በእንስሳ ጤና ላይ ጉዳት የሚስከትል ሲሆን፤
ሠ . በቆይታ ምክንያት የተቀጣጣይነትና መርዛማ ባህሪ ያላቸው ነገሮች ሲሆኑ፤
ረ . በተለያየ ምክንያት ለሌላ በጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር ሳይተላለፍ የቀረ፤
ሰ. በአዋጅ 621/2001 አንቀፅ 77/4 መሰረት የቆይታ ጊዜ ያለፈባቸው የሂሳብ ሰነዶች እና ሌሎች ሰነዶች፡፡
1. ንብረት የማስወገድ ስርዓቶች የሚከተሉትን ያጠ

ቃልላል፡ –
ሀ . ንብረቶችን በጨረታ ወይም ያለ ጨረታ መሸጥ፣
ለ . በሽያጭ ሊወገድ ያልቻሉ ንብረቶች በማቃጠል ወይም በመቅበር፣
2. ልዩ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው የንብረት አወጋገድ ዘዴዎች፡ –
ሀ . መርዛማ ተቀጣጣይ ኬሚካሎች ጊዜ ያለፈባቸው መድሃኒቶች የመሳሰሉት ሲወገዱ የአካባቢ ምህዳርን
በማይበክል ሁኔታና በጥንቃቄ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
ለ . በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ 3/ሀ የተጠቀሰው አወጋገድ በሌሎች

ህጐች የተቀመጡ ድንጋጌዎችን የማያስቀር
ሲሆን የተዛማጅ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ኤክስፐርቶች ባሳተፈ መልኩ የሚፈፀም
ይሆናል፡፡

አንቀጽ 35. የንብረት አስወጋጅ ኮሜቴ አወቃቀር
1. ኮሚቴው የሚዋቀረው በኤጀንሲው ወይም ውክልና በተሰጠው በክልል የበጎ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት
ለመመዝገብና ማስተዳደር በሚመለከታቸው አካላት፡ –
ሀ . ኮሚቴው ከሶስት ያላነሱ አባላት ይኖሩታል፤
ለ . የኮሚቴው አስተባባሪና ፀሃፊ በበጎ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ወይም በክልል የበጎ አድራጐት
ድርጅቶችና ማህበራትን በመምራትና ማስተዳደር በሚመለከታቸዉ አካላት ይሰየማሉ፤
ሐ . የኮሚቴው ስብሰባ ከግማሽ በላይ በተገኙ አባላት ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል፤
መ . የኮሚቴው ውሳኔ በድምፅ ብልጫ ሆኖ እኩል ሲሆን አስተባባሪ ወሳኝ ድምፅ ይኖረዋል፤
ሠ . የኮሚቴ

ው የአገልግሎት ዘመን የሚያልቀው ስራው ሲጠናቀቅ ይሆናል፤ ሿሚው አካል አስፈላጊ ሆኖ
ሲያገኘው ለ2ኛ ጊዜ ማራዘም ይችላል፡፡
አንቀጽ 36. የንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት

1. ንብረት አስወጋጅ ወይም ሽያጭ ኮሚቴው ስለሚወገድ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ይይዛል፤
2. በዚህ መመሪያ በተገለፁት የማስወገጃ መመዘኛዎችና ዘዴዎች የቀረቡ ሰነዶች ይገመግማል፤
3. አስወጋጅ ኮሚቴው ንብረቶቹ ባሉበት ቦታ በመገኘት ለውሳኔ የሚረዳ ግምገማዎች በማድረግ ለሿሚው አካል
የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፤ www.abyssinialaw.com

14 
 
4. አስወጋጅ ኮሚቴው እንዲሸጡ ውሳኔ የተላለፈባቸው ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ ያወጣል በጨረታ ሰነድ ላይ
እንዲገለፅ ያደረጋል፤
5. የጨረታ ሰነድ ያዘጋጃል፤
6. ማስታወቂያ ያወጣል፤ ጨረታ ይከፍታል፤ ያጫርታል፤ የውጤቱንም ሪፖርት ለሿሚው አካል ያቀርባል፡፡

አንቀጽ 37. የንብረት አስወጋጅ ወይም ጨረታ ኮሚቴው ስብጥር

1. ንብረቱ ከሚወገድበት የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር፣ ከኤጀንሲው ወይም ከየክልሉ የበጎ አድራጎትና
ማህበራት ለመቆጣጠር ውክልና ያለው ቢሮ እንዲሁም ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማህበራት ጋር ተዛማጅ
ከሆኑ ዘርፍ አስተዳዳሪዎች የተውጣጣ ይሆናል፡፡
2. የዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ 1 እንደተጠበቀ ሆኖ ኤጀንሲው ለስራው ቅልጥፍናና ወጪ ቆጣቢነት ሲባል በራሱ
ስልጣን ኮሚቴ አቋቁሞ ስራውን ማስቀጠል ይችላል፡፡

አንቀጽ 38. የንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ አባላት ሥነ ምግባር

1. ከማስወገድ ሥራው ጋር በተገናኘ ምንም አይነት የወንጀል ድርጊት አለመፈጸም፤
2. በሚወገደው ኃብትና ንብረት ላይ ምንም አይነት ብክነት እና ምዝበራ አለማድረስ፤
3. ከማስወገድ ሥራው ጋር በተገናኘ ምንም አይነት ሥጦታ ወይም የገንዘብ ዋጋ ያለው ነገር ወይም አገልግሎት
አለመቀበል፤
4. ከማስወገድ ሥራው ጋር በተገናኘ የግድ በምስጢር መጠበቅ ያለባቸውን መረጃዎች ጠብቆ ማቆየት፤
5. በማስወገድ ሥራ ሂደት ሊፈጠሩ የታሰቡ ወይም የተፈጠሩ የሙስና ተግባራትና ብልሹ አሠራሮችን አጥብቆ
መዋጋትና ለሚመለከታቸው የፍትህ አካላት

በየደረጃው ማሳወቅ፤
6. ከማስወገድ ሥራው ጋር በተያያዘ የተፈጠረ ወይም ሊፈጠር የሚችል የጥቅም ግጭትን ለሾመው አካል በጽሁፍ
በማሳወቅ ራሱን ከማጣራት ሂደቱ ማግለል፡፡

አንቀጽ 39. የንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ የሕግ ተጠያቂነት

1. ከንብረት አወጋገድ ጋር በተያየዘ ለሚፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶች የኮሚቴው አባላት በወንጀል ሕግ ድንጋጌዎች
መሠረት ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡
2. በሚወገደው ንብረት ላይ በማሰብም ሆነ በቸልተኝነት ንብረት አስወጋጅ ኮሚቴው ለሚያደርሱት ጉዳት
በፍትሐብሔር ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡

አንቀጽ 40. የሚወገዱ ንብረቶች የጨረታና ሀራጅ ሽያጭ ስነ ስርዓት

1. ኮሚቴው በጨረታ ወይም በሀራጅ የሚሸጡ ንብረቶች ዝርዝር መዝግቦ ይይዛል፤
2. ኮሚቴው በጨረታው ወይም በሀራጅ የሚሸጡ ንብረቶች ለእይታ በሚያመች መንገድ አንዲቀመጡ ያደርጋል፤
3. በጨረታ ወይም በሀራጅ የሚሸጡ ዕቃዎች መነሻ ዋጋ ተምኖ በሾመው አካል ያፀድቃል፤
4. የሚሸጠው ንብረት ማስታወቂያ በጋዜጣ ያወጣል፤
5. በዚህ አንቀፅ ንዑስ ቁጥር 1፣2 ፣3 እንደተጠበቁ ሆነው ኮሚቴው የጨረታ ወይም የሀራጅ ስነ ስርዓትን በተመለከተ
በሌሎች የአገሪቱ ህጐችን ሊጠቀም

ይችላል፤ www.abyssinialaw.com

15 
 
6. በጨረታው ሂደት ቅር የተሰኙ ተጫራቾች ውሳኔው በተሰጠ በሁለት ቀን ጊዜ ውስጥ ለሿሚው አካል በፁሁፍ
አቤቱታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. ሿሚው አካል የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል ፡፡
አንቀጽ 41. ንብረትን ለማስወገድ የሚወጡ ወጪዎች
1. ከማስወገድ ጋር የተያያዘ ማንኛውም ወጪ ንብረቱ በሚወገድለት የበጎ አድራጐት ድርጅት ወይም ማህበር
የሚሸፈን ይሆናል፡፡
2. ሿሚው አካል ያወጣው ወጪ ካለ በሽያጭ ከሚገኘው ገቢ የሚተካ ይሆናል፡፡
3. የሚሸጥ ንብረት ሳይኖር ለማቃጠል ወይም ለመቅበር የሚወጣው ወጪ ንብረቱ በሚወገድለት በጎ አድራጎት
ድርጅት ወይም ማህበር ሊሸፈን የማይችል መሆኑ ሲረጋገጥ ኤጀንሲው ከሚመለከተው የመንግስት አካል
በመመካከር እና በጀት ሲፈቀድለት እንዲወገድ ይደረጋል፡፡

አንቀጽ 42. ከሽያጭ የሚገኘው የተጣራ ገንዘብ በተመለከተ

1. ከሽያጭ የተገኘው ገንዘብ በኤጀንሲው ወይም በክልል በበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት የሚያስተዳድር
አካል ወሳኔ ተመሳሳይ ዓላማ ላለው ወይም ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልገው ብሎ ኤጀንሲው ላመነበት ለበጎ አድራጎት
ድርጅት ወይም ማህበር እንዲውል ይደረጋል፡፡
2. ሳይፈርሱ የንብረት ማስወገድ አገልግሎት እንዲሰጣቸው ለኤጀንሲው ወይም ለሚመለከተው የክልል አካል
ያመለከቱ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ከንብረት ሽያጩ የተገኘው ገንዘብ በኤጀንሲው ወይም ስልጣን
ባለው የክልል መንግስት የሚወሰን

ሆኖ ገቢው ንብረቱ ለሚወገድለት በጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር፣
ወይም ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ አላማ ላለው በጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማህበር ወይም ልዩ ድጋፍ
ለሚያሰፈልገው ብሎ ኤጀንሲው ላመነበት ማንኛውም የበጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማህበር እንዲውል
ይደረጋል፡፡ www.abyssinialaw.com

16 
 
ክፍል ስድስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
አንቀጽ 43. የመሸጋገሪያ ድንጋጌ
1. በአዋጅ 621/2001 አንቀፅ 111/2 መሰረት ዳግም ሳይመዘገቡ በቀሩት በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ሃብትና
ንብረት ላይ አጣሪው የማጣራት፣ ማስተላለፍ እና የማስወገድ ስራውን አጠቃልሎ የሚሰራ ይሆናል፡፡
2. የተጀመሩ (በሂደት ያሉ ) ውሳኔ ያገኙ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት በተጀመሩበት ሂደት እንዲጠቃለሉ
ይደረጋሉ፡፡
አንቀጽ 44. ተጠብቀው የሚቆዩ ሰነዶች
1. የፈረሰ በጎ አድራጎት ድርጅትና ማህበር የንብረትና የሂሳብ መዛግብት ኤጀንሲው ለ 5 ዓመት ጠብቆ የማቆየት
ግዴታ አለበት፡፡
2. እነዚህ ሰነዶች ለማየትና ለመመርመር የሚፈልግ ሰው በኤጀንሲው ዋና ዳሬክተር ሲፈቀድ በደንብ ቁ 168/2001
መሰረት የተወሰነውን ገንዘብ ከፍሎ ቅጅ ሊወስድ ይችላል፡፡
3. ሰነዶቹ ሀገራዊ ጠቀሜታ ላላቸው ጥናትና ምርምሮች እንዲሁም ለፍትህ ስራ ሲፈለግ ያለ ምንም ክፍያ ሊታዩ
ይችላሉ፡፡

አንቀጽ 45.ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው ህጎች
ይህንን መመሪያ የሚቃረን ማንኛውም መመሪያ ወይም ልማዳዊ አሰራር በዚህ መመሪያ በተመለከቱት ጉዳዩች ላይ
ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ አሁን በመጣራት ላይ ላሉ በሕግ የፈረሱ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና
ማህበራት ንብረትን ለማጣራት በተመለከተ መመሪያው አያካትትም፡፡
አንቀጽ46. መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ
ይህ መመሪያ ከነሐሴ 21 ቀን 2003 ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

ዓሊ ሲራጅ መሀመድ
የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ
ዋና ዳይሬክተር
www.abyssinialaw.com