Consortium of Charities and Societies Directive No. 1

For optimal readability, we highly recommend downloading the document PDF, which you can do below.

Document Information:

  • Year:
  • Country: Ethiopia
  • Language: English
  • Document Type: Domestic Law or Regulation
  • Topic:

1

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት
ሕብረት ስለሚመሰርቱበት ሁኔታ የወጣ
መመሪያ
ቁጥር 1/2002

ጥር 15 ቀን 2002www.abyssinialaw.com

2
የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ሕብረት ስለሚመሰርቱበት ሁኔታ የወጣ መመሪያ

1.
አውጪው ባለሥልጣን
የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ ቁጥር 621/2001
አንቀጽ 15 (3) እና አንቀጽ 55 (2) እንዲሁም በደንብ ቁጥር 168/2001 አንቀጽ 34 መሰረት የሚከተለውን መመሪያ
አውጥቷል፡፡

2. አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ “ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ህብረት መመሪያ ቁጥር 1/2002” ተብሎ ሊጠቀስ
ይችላል፡፡

3. ትርጓሜ
በዚህ መመሪያ ውስጥ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጓሜ የሚያሠጥ ካልሆነ በስተቀር፤
1. “አዋጅ ” ማለት የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ለመመዝገብና
ለማስተዳደር የወጣ አዋጅ ቁጥር 621/2001 ነው፡፡
2. “ደንብ ” ማለት የበጎ አድራጐት ድርጅቶች እና ማህበራት ምዝገባ እና
አስተዳደር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 168/2001 ነው፡፡
3. “ኤጀንሲ ” ማለት በአዋጁ አንቀጽ 4 መሰረት የተቋቋመው የበጎ
አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ነው፡፡
4. “ጠቅላላ ጉባኤ ” ማለት የህብረቱ መስራች አባላትና በህብረቱ
መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ተቀባይነት ያገኙ ሌሎች የበጎ አድራጎት
ድርጅቶችን ወይም ማህበራትን በአባልነት ያቀፈ የህብረቱ የበላይ አካል ነው
፡፡
5. “የሥራ አመራር ቦርድ ማለት በህብረቱ ጠቅላላ ጉባዔ የሚመረጥና
የህብረቱን እንቅስቃሴ በቅርበት የሚከታተል አካል ማለት ነው፡፡
6. በአዋጁ አንቀጽ 2 እና በደንቡ አንቀጽ 34 የተሠጡ ትርጓሜዎች ለዚህ
መመሪያም ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
7. “ህብረት ” ማለት በኤጀንሲው ወይም ስልጣን ካለው የክልል መንግስት መዝጋቢ አካል ህጋዊ
ሰውነት ያላቸው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማህበራት የጋራ ሥራቸውንና አላማቸውን
እንዲያስተባብር፤ እንዲሁም በዚህ መመሪያ አንቀጽ 5(2) ሥር የተዘረዘሩ ተግባራትን ለማከናወን
በበጎ አድራጎት ድርጅቶቹ ወይም ማህበራቱ የበላይ አካል ውሳኔ የሚቋቋም ራሱን የቻለ ተቋም
ነው፡፡

4. የመመሪያው ተፈጻሚነት

1. ይህ መመሪያ በኤጀንሲው የሥልጣን ወሰን መሰረት ተመዝግበውና ህጋዊ ሰውነት አግኝተው
በሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማህበራት ህብረቶች ላይ ተፈጻሚ ነው፡፡
2. መመሪያው ህብረት ባልሆኑ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማህበራት ላይ ተፈጻሚነት
አይኖረውም፡፡

www.abyssinialaw.com

3
5. ህብረቶች ስለሚመሰረቱበት ዓላማዎች

1. ህብረቶች የሚመሰረቱት የአባል በጎ አድራጎት ድርጅቶችን ወይም ማህበራትን ሥራና አላማቸውን
ለማስተባበር መሆን ይኖርበታል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ህብረቶች አባል የበጎ አድራጎት
ድርጅቶች ወይም ማህበራት ከተቋቋሙበት ዓላማ ጋር የማይቃረኑ የሚከተሉትን ተግባራትን
ማከናወን ይችላሉ፡፡
ሀ ) ለጋራ ግቦች ስኬታማነት አባሎቻቸውን መደገፍ፣
ለ ) የሀሳብ፣የመረጃ እና የልምድ ልውውጥን ማካሄድ፣
ሐ ) የአባላትን አቅም የመገንባት ተግባራትን ማከናወን፣
መ ) የአባላትን

ሥነ ምግባርና የሙያ ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችሉ ሥራዎችን መስራት እና
ተመሳሳይ ተግባራት፣
ሠ ) የህብረቱ አባላት አላማቸውን ለማሳካት የሚያጋጥማቸውን ችግሮች በመፍታት፣ምቹ
ሁኔታዎችን በመፍጠርና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር ይሰራሉ፡፡
3. ማንኛውም ህብረት ከላይ ከተመለከቱት ዓላማዎች ውጭ እንደ አንድ የበጎ አድራጎት ድርጅት
ወይም ማህበር የበጎ አድራጎት ሥራዎችን የማከናወን እንቅስቃሴ ውስጥ በቀጥታ መሳተፍ
አይችሉም፡፡

6. ህብረት ለመመስረት የሚያስፈልጉ ቅድመ -ሁኔታዎች

በአዋጁና በደንቡ ላይ የበጎ አድራጎት ወይም ማህበር ለማቋቋም የሚያስፈልጉ አግባብነት ያላቸው
መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆኖ ህብረት ለመመስረት የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት
ይኖርባቸዋል፡፡
1. በህብረቱ መስራች አባላት የተፈረመ መተዳደሪያ ደንብ፣
2. ህብረቱን ለመመስረት መስራች አባላት የተስማሙበት ቃለ ጉባዔ፣
3. ከኤጀንሲው ወይም ስልጣን ካለው የክልል መዝጋቢ አካል የተሰጠና የታደሰ የምዝገባ
ሰርተፊኬት፣
4. እያንዳንዱ የህብረቱ አባል በየራሱ የበላይ አካል ህብረቱን ለመመስረት ወይም የህብረቱ አባል
ለመሆን

ውሳኔ ያስተላለፈበት ቃለ ጉባዔ፣
7. የህብረት መተዳደሪያ ደንብ መያዝ ስለሚገባቸው ፍሬ ነገሮች

በአዋጁ አንቀጽ 68 እና በደንቡ አንቀጽ 6 ላይ የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር መተዳደሪያ
ደንብ መያዝ ያለባቸው አግባብነት ያላቸው መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆኖ የህብረት መተዳደሪያ ደንብ
የሚከተሉት በተጨማሪነት መያዝ ይኖርበታል፡፡
1. አባላትን የሚቀበልበት ሥርዓት፤
2. ስለ አባላቱ መብትና ግዴታዎች፤
3. አባልነት ስለሚቋረጥበት ሁኔታዎች፤
4. የጠቅላላ ጉባዔው ድምጽ አሰጣጥና የሥብሰባ ሥነ ሥርዓት፤
5. ¾ጠቅላላ ጉባዔ የ U`Ý“ ¾¨